House and Building Sale

በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ (መ/ቁ/102803) የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ወረዳ 25 በአዲሱ ወረዳ 13 የሚገኝ የቦታ ስፋቱ 694.88 ካ/ሜ የሆነ ድርጅት ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት አለም መካ እና የፍ/ባለዕዳ እነአቶ ወልዴ በረካ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/102803 በ2/10/2015ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/107090 በ11/11/2015ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/107090 በ14/5/2017ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በቀድሞ 25 በአዲሱ 13 ውስጥ የሚገኝ የካርታ ቁጥር ወ13/ውዝ01/66/2199/00 የቤት ቁጥር 001 የሆነ በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን የቦታ ስፋት 1,247.46ካ/ሜ ሲሆን በአስኮ ሚኪሊ ላንድ መንገድ ፕሮጀክት ምክንያት በከፊል የፈረሰ እና ካሳ የወሰዱ እና ከ1,247.46 ካ/ሜ ላይ 448.76 ካ/ሜ የተቀነሰባቸው ቢሆንም በ39/40ኛ ዙር መንገድ ጥናት እና በአስኮ ሚኪሊለንድ መንገድ ፕሮጀክት ዲዛይን መሻሻሉ ምክንያት ካሳ ያልተከፈላቸው እና 2ኛ ዙር የሚቀነስባቸው የቦታ ስፋት 103.82ካ/ሜ የሚቀነስባቸው ሲሆን ቀሪው የቦታ ስፋት 694.88ካ/ሜ ቤት ድርጅት ስለሆነ ካፒታል ጌን ታክስ የሚከፍለው የፍ/ባለዕዳ ሲሆን ገዥው አካል ቤቱን የሚረከበው የክ/ከተማው መሬት አስተዳደር በላከው እስኬች መሰረት ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 44,420,669.95 (አርባ አራት ሚሊዮን አራት መቶ ሃያ ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ከ95/100 ) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 7 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የፌደራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-16
  • Bid closing time: 11:30
  • Bid opening: 2026-11-16 11:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Oct 15, 2026)
  • Posted at: 2026-10-15T08:04:33.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders