House and Building Sale

በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ (ኮ/መ/ቁ/113218) በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የሚገኝ የቦታ ስፋቱ በሰነድ 45.94 ካ/ሜ (ጠቅላላ በፕሮፖርሽን 53.94 ካ/ሜ) የሆነ የቤት ቁጥር 407 የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት እነ ትዕግስት በቀለ እና የፍ/ባለዕዳ እነ አልጋነሽ ዘለቀ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጋሞ ዞን የጬንቻ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 18933 በ25/10/2016 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/113218 በሐምሌ 25 ቀን 2017ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 407 በሴሪያል ቁጥር 008420 የካርታ ቁጥር አከ-08/2711/3407/አ.ካርታ በተመኔ ቱንጋ እና የዘለቀ ተካ ወራሾች ስም የተመዘገበ የቦታ ስፋቱ በሰነድ 45.94 ካ/ሜ ጠቅላላ በፕሮፖርሽን የሚደርሰው 53.94ካ/ሜ የሆነ በአካባቢው የውስጥ ለውስጥ መንገድ 2.ካ/ሜ ይነካዋል አዋሳኞቹ በስተሰሜን ቤት ቁጥር 410 በስተደቡብ መንገድ /ባዶ ቦታ በስተምዕራብ መንገድ/ባዶ ቦታ በስተምስራቅ ቤት ቁጥር 408 የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 2,675,494.44 ( ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ አራት መቶ ዘጠና አራት ብር ከ44/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 7 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.PO አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-16
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-11-16 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Oct 15, 2026)
  • Posted at: 2026-10-15T08:20:07.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders