Textile, Garments and Uniforms

የአዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ግዢ እና ንብረት ኣስተዳደር ለ2019 አ.ም በጀት ኣመት ቁጥር 001/2019 አገልግሎት ላይ የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የእቃው ኣይነት

ሎት

 

የሚያሲዘው የብር መጠን እና ፐርሰንት

 

1

የደንብ ልብስ

 

1

10,000.00 1 ፐርሰንት

 

2

አልባሳትና የወለል ምንጣፎች

2

4,000.00 0.8 ፐርሰንት

 

3

የደንብ ልብስ ስፌት

 

3

7,000.00 1 ፐርሰንት

 

4

አላቂ የጽዳት እቃዎች

 

4

8,000.00 1 ፐርሰንት

 

5

አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች

 

5

8,000.00 0.9 ፐርሰንት

 

6

አላቂ የቢሮ እቃዎች

 

6

10,000.00 0.8 ፐርሰንት

 

7

የትምሀርት መርጃ መሳሪያዎች

 

7

6,000.00 0.8 ፐርሰንት

 

8

ቋሚ እቃ

 

8

15,000.00 2 ፐርሰንት

 

9

የጥገና ስራዎች

 

9

5,000.00 0.8 ፐርሰንት

 

10

የመምህራንና ሰራተኛ የሻይ ክበብ (ካፌ)

10

10,000.00 2. ፐርሰንት

 

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታ እዲሳተፉ ይፈልጋል።

  1. የንግድ ፍቃድ የምዝገባ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)ያላቸው 100000 /ከኣንድ መቶ ሺ ብር በላይ የሆነ ግዢና ኣገልግሎት ቫት ተመዝጋቢ መሆን ኣለበት ተጨማሪ እሴት ታክስ( ቫት) ተመዝግቢ የሆኑና በኣቅራቢነት የተመዘገቡ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ለካፌ ተወዳዳሪዎች ብቻ ለኣንድ ጊዜ ተጨማሪ እሴት ታክስ (  ቫትን) ኣይጠይቅም። ተጫራቾች በተሰጣቸው ንግድ ዘርፍ የስራ ፍቃድ ብቻ መሳተፍ የሚችሉ መሆን ኣለባቸው በዌብሳይት የተመዘገበ ለካፌ ተጫራች እና ለጥገና በኣቅራቢነት ያልተመዘገቡ ቢሆኑም መወዳደር ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በተፈቀደላቸው ዘርፍ ላይ ብቻ ስለሆነ ሰነድ በነጻ የሚሰጣቸው የተፈቀደላቸውን ዘርፍ ፍቃድ ኮፒ ማምጣት ሲችሉ ብቻ ነው።
  2. ተጫራቾች ማንኛውንም የመንግስት ታከስና የግብር ግዴታዎች ከነ መጓጓዣው በሚያቀርበው የመወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውሰጥ ኣካቶ ማቅረብ ኣለበት ነጠላ ዋጋውን ከነቫቱ ማስቀመጥ የሚቻለው የጨረታ ሰነዱላይ ባለው ቦታ ብቻ ሲሆን ከዓንድ በላይ ዋጋ የሚያቀርቡበት ካለ ግን ኮፒ በማድረግ ሁለተኛ ገጽላይ ጽፈው ኣያይዘው ማቅረብ ይችላሉ። እንዲሁም ዋጋ ከነቫቱ እስቀምጡ ተብሎ በተጻፈው መሰረት የተቀመጠውን ዋጋ ከነቫቱ እንደሆነ ነው የምንወስደው። ምክንያቱም የኣንዱ ነጠላ ዋጋ ከነቫቱ ስለተጠየቀ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ(CPO)ከላይ በተዘረዘሩት ሎቶች መሰረት ለእያንዳነዱ በተቀመጠው የብር መጠን መሰረት ወይንም የተወዳደሩበትን የጠቅላላ ዋጋ 0.5-2 ፐርሰንት ድረስ ከላይ በየሎቱ በተቀመጥው የብርና የፐርሰንት መጠን በኣዲስ ከተማ መሰናዶ ት/ቤት ስም የተዘጋጀ በባንከ በተረጋገጠ (CPO)ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ኣነስተኛ እና ጥቃቅን ተወዳደሪዎች ከሆኑ ደግሞ ህጋዊ ካደራጃቸው ተቋም የጨረታ ማስከበሪያ ወይንም ካሸነፉ ቡሃላ የውል ማስከበሪያ ህጋዊ የሆነ ደብዳቤ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።
  4. እንዲሁም ተጫራቾች ጨረታውን እነዳሸነፉ ከተገለጸላቸው ቡሃላ በሚጠቀስው የገንዘብ መጠን ልክ ኣጠቃላይ የዋጋውን 10 ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ ማምጣትና መዋዋል ይጠበቅባቸዋል እንዲሁም ኣሸናፊዎች ከተገለጸላቸው ቡሃላ እቃው ጠፍቷል እቃው ሙግባት ኣይችልም ወይንም ገና ሊመረት ነው ወይንም ዋጋ ስለጨመረ እና እንዲሁም ተመሳሳይ ያልሆነ እቃ ለመስገባት መሞከር ተጠያቂነትን ያስከትላል በተጨማሪም ኣነስተኛና ጥቃቅን ተጫራች ከሆኑ ላደራጃቸው ወይንም ዋስትና በኣድራሻችን ጽፎ ደብዳቤ ለላከው ተቋም ኣስፈላጊውን የተጠያቂነት ፎርም ሞልተን እንደምናሳውቀው እና ለሚመለከተው ኣካል የም ናስተላልፍ መሆኑን ኣውቀው ሁሉም ተጫራቾች ከወዲሁ የጨረታውን ጥራት ጠብቀው መወዳደር ይጠበቅባቸዋል ።
  5. ጨረታ ሰነድ በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል በግንባር በመቅረብ ለዚሁ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኣካውንት ቁጥር 1000012608903 በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 10 መውሰድ ይኖርባቸዋል ።
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ሳንምፕል ጨረታ ከመከፈቱ 3 ቀን በፊት ኣስቀድሞ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ሳምፕል የሚያስገባ ተወዳዳሪ በኣስራ ኣንደኛው ቀን ቢያመጣ የማንቀበል መሆኑን ከወዲሁ ኣውቆ ከመከፈቱ ከ3ቀን በፊት ማስገባት እንዳለበት እያሳወቅን ሳንምፕል ለማይቀርብባቸው እቃዎች ት/ቤቱ ድረስ በመምጣት ሳምፕሉን በማየት የጥገና ስራዎችን እና በስፌስፊኬሽኑ መሰረት የተጠየቁ እቃችዎን ማቅረብ ይቻላል ሌላው በመዝጊያና በመከፈቻ ቀን የሚመጡ ሳምፐሎችን የማንቀበል መሆኑን በድጋሚ እናሳውቃለን። በተጨማሪ ናሙና ማቅረብ አስቸጋሪ ለሆኑ ወይንም ክብደት ላላቸው እቃዎች የሚወዳደሩበትን እቃ እስፔስፊኬሽን ወይንም ፎቶ ማቅረብ ይችላሉ። ነገርግን የኮምፒተር ናሙና እቃው በኣካል መቅረብ አለበት እንዲሁም በተጨማሪ የንግድ ቦታድረስ በመሄድ የሚታይ ይሆናል።
  7. ለውድድር ያስገበትን ናሙና ጨረታው እደተጠናቀቀ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ሳይወስዱ ግን እስከ 6 ወር ድረስ ከቆዩ ላስገቡት ናሙና እና ማንኛውንም ነገር የማንጠየቅ እና ሃላፊነት መውሰድ የማንችል መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን ምክንያቱም የኣገልግሎትቀኑ ሊያልፍና ሊበላሽ ሊቀደድ ስለሚችል።
  8. ተጫራቾች የንግድ ፍቃዳቸውን የምዝገባ ፍቃድ ቫት ቲን የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ንግድ ፍቃድ ያደሱና በኣቅራቢነት የተመዘገቡበትን ሰነድ ሙሉ የዋጋ ዝርዝራቸውን ጭምር በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ የሁሉንም ሰነድ ኣንድ ኦርጅናልና ኣንድ ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ዋናና ኮፒ ቴክኒካል ዋናና ኮፒ በኣራት ፖስታ በማድረግ እንዲሁም ሙሉ የጨረታ ሰነዱን በያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ይመለሳል። ይህ ማስታቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰኣት በት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታውን ሰነድ በመሙላትና በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከተፈቀደው ዋናና ኮፒ ሰነዶች ቀንሶ ማስገባት ኣይፈቀድም። እንዲሁም ዋናላይ የሚገቡ ሰነዶች ኮፒላይ በስህተት ቢገባም ከኮፒ ውስጥ ሰነድ ወጥቶ እንደኦርጅናልተከፍቶ ሊታይለት ኣይቻለም ሊወዳደርበትም የማይችል መሆኑን እንገልጻለን። በሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆነ ወይም ስርዝ ድልዝ መረጃ ተቀባይነት የለውም።
  9. የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ 11 ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3.00 ሰኣት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን በት ቤቱ መሰብሰቢያ ኣዳራሽ ውስጥ ከጠዋቱ 3.30 ሰኣት ላይ ይከፈታል። ተጫራቾች ጨረታ ላይ መገኘት ካልቻሉ ህጋዊ ወኪሎቻቸውን መላክ ይችላሉ። ተጫራቾች ወይንም ሀጋዊ ወኪሎቻቸው ካልተገኙ መስፍርቱን ካሟሉ ባይገኙም ያልተገኙትም ተጫራቾ ፖስታ ጭምር ይከፈታል። የጨረታ ኣከፋፈት ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ዝግ የሆኑ ቀናቶች ከገጠመ በሚቀጥለው ከፍት የስራ ቀን በተቀመጠው ሰኣት ይከፈታል። ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው እንደተገለጸ ወዲያውኑ በመቅረብ እቃውን ከማስገባቱ በፊት የአጠቃለይ ያሸነፈባቸውን እቃ ዋጋ ኣስር ፐርሰንት ብር (CPO)ከላይ በተጠቀሰው ስም ከባንክ በማሰራት ውል በመዋዋል ያሸነፉባቻውን እቃዎች ግዢ ፈጻሚው መስሪያቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች እንዳሸነፉ ከተገለጸላቸው ቡሃላ በትእዛዝ ከሚሰሩ እቃዎች ዊጪ እቃ እጄላይ የለም ቀጠሮ ይሰጠን በሚል የተለያዩ ምክንያቶችን ማቅረብ ኣይፈቀድም ምክንያቱም እጅ ላይ ባለ እቃ ነው መወዳደር የሚችሉት ይሀ ሳይሆን ቢቀርና ማሸነፋችሁ ከተገለጸ ቡሃላ እቃ ጠፍቷል ጊዜ ስጡኝ የሚል ጥያቄ ኣናስተናግድም መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት እንጠይቃለን። ሌላው ደግሞ ማንኛውንም እቃ ከ9 ሰኣት ቡሃላ ጭነው ቢመጡ የማንቀበል መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን ምከንያቱም ጥራት ኮሚቴ ኣይቶ ፍትሾ ስለሚያስገባ ሰኣት ስለሚያጥር ነው።
  10. ት/ምርት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ወይንም ከ20 ፐርሰንት በላይ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።


አድራሻ ኣዲስ ከተማ የክፍለሃገር ኣውቶብስተራ አጠገብ የሚገኘው ኣዲስ ከተማ
አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 276 3811/15/17
በኣዲስ ከተማ ክፍለከተማ ኣስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኣዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት / ቤት
ኣጠቃላይ ማሳሰቢያ የካፌ ፤የዴክስ፤ የመስኮትና፤ የቆርቆሮ፤ የላሜራ
በሮች፤የቧንቧ ስራዎች፤አሸንዳና ጎራንዳዮ የመሳሰሉት በኣንድ ጎራ ላይ የሚሰሩስራዎች በሙሉ ባጠቃላይ ድምር ውጤት ነው ኣሸናፊው የሚገለጸው።
እንዲሁም ለካፌ ተወዳዳሪዎች የቤት ኪራይ ብር 10,000.00(አስር ሺ ብር) እና የዴስቲቪ ክፍያ በተጫራቹ የሚከፈል ነው።
የካፌው ኣሸናፊው የሚለየው በጨረታ ሰነድ ላይ በቀረቡት ዝርዝር የኣገልግሎት ኣቅርቦት
ተጫራቾች በሞሉት ዋጋ ድምር ነው
የካፌ ተወዳዳሪ ኣሸናፊዎች ካሸነፉ ቡኃላ ሙሉ የሚያገለግለው ለሶስት ወር ብቻ ነው
ለበጀት ኣመቱ በየሶስት ወሩ ሙሉ ይታደሳል ።
የትራንስፖርት እና የጥገና ኣገልግሎት ስራዎች ካሸነፉ ቡሃላ ለበጀት ኣመቱ ሙሉ ነው።

የአዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-27
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰኣት
  • Bid opening: 2026-10-27 09:30
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰኣት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ketema Education Office Addis Ketema Secondary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 15, 2026)
  • Posted at: 2026-10-15T08:38:42.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders