Freight Transport

ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢዎችን በተባባሪነት (Sub-Contract) አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ውል መግባት ይፈልጋል

Description

ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት

የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ጨረታ

ጨረታ ቁጥር ዕ / ደ / ዕ / ት / ድ/002/2019

ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት በዘርፉ ልምድ ያላቸውን ህጋዊ የግል ትራንስፖርቶችን በተባባሪነት በማስገባት/Sub Contract/ የጭነት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ለአንድ ዓመት ውል በመግባት አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች በተመለከተ ከዚህ በታች በዝርዝር ቀርቧል፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የተከፈለበት/ Tax clearance/
  2. በዘርፉ የተሰማራበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፤ እንዲሁም የንግድ ምዝገባ
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin)
  4. ቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  5. የመንግስት ግዥ ባለስልጣን የተመዘገቡበት (Egp Regstration)
  6.  የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ከፋይናንስ ዲፓርትሜንት መግዛት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች በቀረበው የአገልግሎት ግዥ ዝርዝርን መሠረት በማድረግ የሚወዳደርበትን ነጠላ ዋጋ (unit Price) እና ጠቅላላ ዋጋ (Total price) በግልፅ በሚነበብ አሃዝ በማስቀመጥ ከነቫቱ በመሙላት የጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት አስቀድሞ ድርጅቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
  8. የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የኦፕሬተር የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
  9. የባለቤትነት ማረጋገጫ (ሊብሬ) ያላቸውና ኮፒው ላይ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ ማቅረብ የሚችሉ፤
  10.  የጭነት አገልግሎት መስጠቱን የሚያረጋግጥ የሚገልጽ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማስረጃ ከሶስት እና ከዚያ በላይ ድርጅት የተሰጠ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ አለባቸው፤
  11. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ተሽከርካሪዎች አጠቃላይ የመድን ዋስትና የተገባላቸው ስለመሆኑ የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል፤
  12. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ በባንክ በተመሠከረ የክፍያ ትዕዛዝ  (CPO) ወይም ህጋዊ የባንክ ዋስትና ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር)፤ በታሸጎ ፖስታ አድርገው በዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት (Emergency Relief Transport Enterprise) ስም በማዘጋጀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  13.  የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ይሆናል፡፡
  14.  ተጫራቾች ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በመሙላት ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኦርጅናል፣ ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኮፒ ፋይናንሽያል ኦርጅናል ፣ ፋይናንሽያል ኮፒ በማድረግ ለይተው በተለያየ ፖስታ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም በማሳረፍ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
  15.  በቴክኒካል ፕሮፖዛል ግምገማ ያለፈ ተጫራች በፋይናንሻያል ሰነድ አከፋፈት ላይ እንዲገኝ ጥሪ ይደረግለታል፡፡
  16. የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተከትሎ ተጫራቾች የታሪፍ ማሻሻያ ጥያቄ ማቅረብ የሚችሉት በውል ጊዜ ውስጥ የተደረገው የዋጋ ጭማሬ 20% እና ከዚያ በላይ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው፤
  17. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 400 ኩንታል የመጫን አቅም ያለውን ተሽከርካሪን ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
  18. በተጫራቹ የሚቀርበው ዋጋ በኢትዮጵያ ብር ይሆናል፤
  19. የጨረታ ማቅረቢያ ሠነዶች በሙሉ በአማርኛ ቋንቋ ተፅፈው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  20. ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት 10 የስራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በዛውኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ይከፈታል፤ ነገር ግን የጨረታ መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተገለፀው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል፤ እንዲሁም በጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ሣይገኙ ቢቀር ጨረታው ይከፈታል፤
  21. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

የድርጅቱ የሥራ ሰዓት

  • ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡0o ሰዓት - 6፡00 ሰዓት
  • ከሰዓት ከ7፡00 ሰዓት – 11፡00 ሰዓት ቅዳሜ እስከ 10:00

በስልክ ቁጥር 0114390075/1569/3592/0114391027

ፋክስ 0114-39-63-36 ፖ.ሳ.ቁ.2562  አዲስ አበባ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት አሁን አሁን ትሬን ባትሪ መሸጫ ህንጻ በስተጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ ነው።

ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-26
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት 10 የስራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በዛውኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-26 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት 10 የስራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በዛውኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Elet Derash Relief Transport Enterprise
  • Buyer address: አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት ትሬን ባትሪ መሸጫ ህንፃ ጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ
  • Bid bond: 500,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 15, 2026)
  • Posted at: 2026-10-15T09:38:31.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders