Stationery

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡኢ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅህፈት ቤት ለተለያዩ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚሆን የፅህፈት መሳሪያ በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ባላቸው አካላት በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ 01/2019 ዓ.ም

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡኢ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅህፈት ቤት ለተለያዩ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚሆን የፅህፈት መሳሪያ በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ባላቸው አካላት በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. የዘመኑ ግብር የከፈለ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣

2. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው፣

3. ቲን-ነምበር ያለውና ቫት VAT ተመዝጋቢ የሆነ

4. ጨረታው የሚቆየው ከ 6/2/2019 ዓ.ም እስከ 16/02/2019 ዓ.ም ባሉት ለተከታታይ ቀናት ሲሆን ተጫራቾች ዋጋቸውን በመሙላት የግ/ን/አስ/ስ/ሂደት ቢሮ ቁ/ር 5 በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ17/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ቡኢ/ከ/አ/ፋ/ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ስ/ሂደት ቢሮ ቁ/ር 5 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።

6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ ዋስትና የባንክ (CPO) ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።

7. የጨረታ ማስከበሪያው ለተሸናፊው ድርጅት አሸናፊው ውል መግባቱን ከተረጋገጠ በኋላ ይመለስለታል።

8. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱን ከተረጋገጠ እስከ ቡ/ከ/አ/ፋ/ጽ/ቤት በመቅረብ ውል መፈጸም ይኖርበታል።

9. አሸናፊው ድርጅት ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ሲፈጽም በግዥ መመሪያው መሰረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅበታል።

10. ተጫራቾች የስራው ዝርዝር የያዘ ሰነድ ቡኢ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6, በመቅረብ የሰነድ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይቻላል።

11. አሸናፊው የሆነው ድርጅት ያሸነፋቸው እቃዎች እስከ ቡኢ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅህፈት ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልታችሁ ስታስገቡ 1 ኦርጂናል 2 ፎቶ ኮፒ በማድረግ በሁለት ፖስታ ለይታችሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። /ሲፒኦ ለብቻው በፖስታ

13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0468830750/769 በመደወል ማረጋገጥ ይቻላል።

በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡኢ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅህፈት ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-27
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-10-27 14:30
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Buee City Administration FEDB
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 16, 2026)
  • Posted at: 2026-10-16T07:43:22.000Z
← Back to all tenders