Textile, Garment and Leather

በባሌ ሮቤ በጎባ ክ/ከተማ የሃጅ ኣደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቢሮ፣ የደንብ ልብስ፣ ለስልጠና እና ለተለያዩ ለምርት ስራ አገልግሎቶች የሚውሉ ቋሚ እና አላቂ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ለሁለተኛ (2) ጊዜ የወጣ

የጨረታ ማስታወቂያ

በባሌ ሮቤ በጎባ ክ/ከተማ የሃጅ ኣደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቢሮ፣ የደንብ ልብስ፣ ለስልጠና እና ለተለያዩ ለምርት ስራ አገልግሎቶች የሚውሉ ቋሚ እና አላቂ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ተጫራቾች፣

1 ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆኑንና የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ፎቶ ኮፒውን ከጨረታው ሠነድ ጋር ማቅረብ የሚችል።

2. ከላይ ለተጠቀሰው እቃ የማወዳደሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50000 (ሀምሳ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ በሃጅ ኣደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3. አሸናፊው የሚያቀርበው እቃ መስፈርቱን የማያሟላ ሆኖ ከተገኘ ለመመለስ ግዴታ የሚገባ መሆን አለበት።

4. የሚቀርቡት ሰነዶች ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።

5. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት የጨረታው ሠነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ከታሸገ በኋላ በዚው ዕለት 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

6. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመግዛት ከጎባ ከተማ ሃጅ ኣደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ።

7. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. የአሸናፊ አቅራቢዎች የውል ማስከበሪያ የእቃውን ሙሉ ዋጋ 10% ኮንትራት አማውንት (በባንክ የተረጋገጠ በሲፒኦ ብቻ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች እቃውን የማጓጓዣ መጫኛና ማውረጃ ወጪውን በመቻል ጎባ ከተማ ሃጅ ኣደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

10. የእቃዎቹን ዋጋ መስሪያ ቤቱ የሚከፍለው በጥያቄው መሰረት መቅረቡ እና ንብረት ክፍል ገቢ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው።

11. ተጫራቾች በቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ጨረታውን ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው በ 5 (አምስት) ቀን ውስጥ መስሪያ ቤቱ ቀርበው ውል መፈረም ይኖርባቸዋል።

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡-

  • እቃ ለማቅረብ የምትወዳደሩ በሙሉ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገባችሁበትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒውን ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ አለባችሁ።
  • ለበለጠ መረጃ ጎባ ከተማ ሃጅ ኣደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በስልክ ቁጥር፡- 0920379891 ወይም 0913181413 መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በባሌ ሮቤ በጎባ ክ/ከተማ የሃጅ ኣደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-28
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-28 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Haji Adem Poly Technic College
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 16, 2026)
  • Posted at: 2026-10-16T08:03:39.000Z
← Back to all tenders