House and Building Sale

የቦታ ስፋት 190 ካ.ሜ የሆነ ቤት ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ
ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍርድ ባለመብት እነ አቤል ተስፋዬ እና በፍርድ ባለእዳ እነ አሰገደች ሀይሌ መካከል ስላለው አፈፃፀምየፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 315105 በቀን 20/5/2017 ዓ.ም እና 330233 በቀን 20/05/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 278-280 የቀድሞ ካርታ ቁጥር 003/1/12289 የነበረው በካዳስተር ምዝገባ ስርዓት መሰረት የይዞታልዩ መለያቁጥርAA000020301295 የተቀየረ በእነ አማረች ዥንጌ አንደግቤ ስም የተመዘገበ የቦታ ስፋት 190ካ.ሜ የቤቱ የሽያጭ ዋጋ መነሻ ግምት ብር 8,446,620 (ስምንት ሚሊየን አራት መቶ አርባ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ሀያ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ/ም ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.330233 በቀን 25/01/2019 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በድጋሚ ሐራጅ ጨረታ ሆኖ 1/4ኛ ብር 2,111,655 (ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ አምስት) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 8 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትጵዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O. ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.P.O. የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-17
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-11-17 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Oct 16, 2026)
  • Posted at: 2026-10-16T08:05:47.000Z
← Back to all tenders