Textile, Garment and Leather

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የ12ኛ ዕዝ ግዥ ክፍል በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የ12ኛ ዕዝ ግዥ ክፍል በ2019 በጀት ዓመት በሎት 1 የተለያዩ የስራ ልብሶችና ጫማዎች በሎት 2 የተለያዩ የጽህፈት እቃዎች፤ በሎት 3 የተለያየ የትምህርት መርጃ እቃዎች፣ በሎት 4 የተለያዩ ቀለቦች፣ በሎት 5 የተለያዩ የፅዳት እቃዎች፣ በሎት 6 የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋዎጫ እቃዎች፣ በሎት 7 የተለያዩ አላቂ የተሽከርካሪ መለዋዎጫ እቃዎች፣ በሎት 8 ተለያዩ የኤሌክትሮኒከስ መለዋወጫ እቃዎች፣ በሎት 9 የተለያዩ የጀነሬተር መለዋዎጫ እቃዎችን፣ በሎት 10 የተለያዩ ለቤት ጥገና የሚውሉ የግንባታ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተጫራች ማሟላት የሚገባቸው

1. ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፣

2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

3. የተጨማሪ አሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

4. የግብር ከፋይ ምዝገባ (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል፤

5. የዘመኑ ግብር የከፈሉ/ከኢትዮ ገቢዎችና ጉምሩከ ባለስልጣን/በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

6. ተወካይ ከሆነ /ከሆነች/ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

7. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያው የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

8. ተጫራች የአንዱን ዋጋ ቫት ሳይጨምር በመሙላት አባዝቶ እና ወደ ታች ደምሮ ከሰራ በኋላ የቫት ድምር ለብቻ መቀመጥ አለበት።

9. የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በእያንዳንዱ የእቃ ዝርዝር በተናጠል ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ እየሆነ ይመጣል።

10. በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። ፍሎድ ከተጠቀሙ ሰነዱ ከውድድር ውጭ ይሆናል።

11. ተጫራቹ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ሲያቀርቡ ኦርጅናል ኮፒ ብለው መለየት ይኖርባቸዋል። ኦርጅናሉን ፋይናንሻል ለብቻ በማሸግ ኮፒውን ፋይናንሻል ለብቻ በማሸግ እንዲሁም በየዘርፉ ከተራ ቁጥር 1-6 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በብቻው በአንድ ፖስታ በማሸግ በመጨረሻ ሶስቱንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ አሽጎ የሚወዳደርበትን ዘርፍ በመፃፍ ማቅረብ አለበት።

12. ለጨረታ ማስከበሪያ ባቀረቡት ዋጋ ልክ 2% በክፍያ ማዘዣ C.P.O ማስያዝ የሚችል መሆነ አለበት።

13. የጨረታ አሸናፊዎች ለውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ 10% የክፍል ማዘዣ C.P.O ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።

14. የጨረታ ሰነዱን ወልድያ በሚገኘው ከ12ኛ ዕዝ ፋይናንስ ቢሮ በስራ ቀንና ሰዓት ከ06/2/19.ዓ/ም ጀምሮ እስከ 17/2/19 .ዓ/ም ድረስ የሚጫረቱበትን የመጫረቻ ሰነድ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

15. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በ18/2/19 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 7፡00 ሰዓት ድረስ ወልድያ በሚገኘው የ12ኛ ዕዝ ቢሮ በር ላይ በሚዘጋጀው ሳጥን ስነዱን ማስገባት አለባቸው። በቀን 18/2/2019 ዓ/ም ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት አዳራሽ ከቀኑ 7፡00 ላይ ጨረታው ይከፈታል።

16. አሸናፊ የሆነው ተጫራች በሚሰጠው የዕቃ አቅርቦት ትዕዛዝ መሰረት ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ዕቃውን አሟልቶ ማቅረብ የሚችል እና በዕዙ የጥራት ኮሚቴ ጥራቱን አረጋግጦ ማስረከብ አለበት። የጥራት ኮሚቴው ካልተቀበለው ቀይሮ የማቅረብ ግዴታ አለበት።

17. አሸናፊ የሆነው ነጋዴ ክፍያ በሚጠይቅበት ጊዜ ህጋዊ ደረሰኝ ከካሽ ሪጅስተር ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት።

18. ዕዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

19. ግዥ ክፍሉ በጀቱን በማረጋገጥ በዘርፋ 20% የመቀነስም ሆነ 20% የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

20. በዚህ ማስታወቂያው ያልተገለፁ ሌሎች ህጎች በሀገሪቱ የግዥ አፈፃፀም መምሪያ መሰረት ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል።

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የ12ኛ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-28
  • Bid closing time: 13:00
  • Bid opening: 2026-10-28 13:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Ministry of Defense
  • Buyer address: መከላከያ ት/ስልጠና ዋ/መ/ግዥ ቡድን ጃል ሜዳ ታቦት ማደሪያ ፊት ለፊት
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 16, 2026)
  • Posted at: 2026-10-16T08:10:53.000Z
← Back to all tenders