House and Building Sale
የቦታው ስፋት 135.28 ካ.ሜ. የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ ባለመበት አቶ ፋንታሁን ገ/ሚካኤል እና የፍ ባለዕዳ ወ/ሮ ሀረጓ ቦጋለ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ/132503 30/07/2016 ዓ/ም በሰጠው ፍርድ እና በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ 142470 በቀን 14/08/2018 በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ለማስፈጸም በኮ ከ ከተማ ወረዳ 02 በሰሜን አቶ ንዋይ የሸዋሉል በምስራቅ የአመልካች ቤት በምዕራብ ወንዝ በደቡብ እቶ ካፒታል ካዜሮ የሚያዋስን ሰነድ አልባ የቦታው ስፋት 135.28 ካ.ሜ. የሐራጅ መነሻ ዋጋ 3,138,300 (ሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ ስምንት ሺህ ሶስት መቶ ሆኖ የታራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 9 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመሰኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት ¼ ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ አፈ ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ አፈ ጽ ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልጻለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852
በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻልን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ / ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-18
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-11-18 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Oct 17, 2026)
- Posted at: 2026-10-17T07:36:21.000Z