Textile, Garments and Uniforms

የቅዱስማርቆስ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የቅዱስማርቆስ ቅድመ አንደኛ አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት ግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ደጋፊ የስራ ሂደት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች 1ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሎት ቁጥር

የእቃው አይነት

ሎት1

ደንብ ልብስ

ሎት2

አላቂ የቢሮ እቃ

ሎት3

ህትመት

ሎት4

የህክምና እቃ

ሎት 5

አላቂ የትምህርት እቃ

ሎት 6

የጽዳት እቃዎች

ሎት 7

ልዩ ልዩ መሳሪያዎች እቃዎች

ሎት 8

ቋሚ የኮፕውተር ጥገና እና ሰርቭስ

ሎት  9

ቋሚ የቢሮ እቃ ( ፕላንትና ማሽነሪ ግዥ)

ሎት 10

ቋሚ የቢሮ እቃ (የህንፃ ቁሳቁስ ተገጣጣሚዎች ግዥ)

ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. የአገር ውስጥ ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የአገር ውስጥ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ከሪላንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው እና የ2019 ዓ.ም በጀት አመት የታደሰ የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸዉ።
  4. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸዉ።
  5. ናሙና በሚያስፈልጋቸው እቃዎች የሚወዳደሩ ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የእቃዉን ናሙና በዝርዝር ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለባቸዉ።
  6. ተጫራቾች ጨረታ ማስረከቢያ ጠቅላላ ዋጋ፡-
    • ሎት 1 ደንብ ልብስ 5000.00 (ኣምስት ሺህ ብር)
    • ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃ 5000.00 (አምስት ሺህ ብር)
    • ሎት 3 ህትመት 2000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
    • ሎት 4 የህከምና እቃ 3000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
    • ሎት 5 አላቂ የትምህርት እቃ 5000.00 (አምስት ሺ ብር)
    • ሎት 6 የጽዳት እቃዎች 5000 (አምስት ሺህ ብር)
    • ሎት 7 ልዩ ልዩ መሳሪያ እቃዎች 5000(አምስት ሺህ ብር)
    • ሎት 8 ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃ ጥገናና እና ሰርቪስ
    • ሎት 10 ቋሚ የቢሮ እቃ ( ፕላንትና ማሽነሪ ግዥ) 5000.00 (አምስት ሺህ ብር)
    • ሎት 11 ቋሚ የቢሮ እቃ (የህንፃ ቁሳቁስ ተገጣጣሚዎች ግዥ) 5000.00 (አምስት ሺህ ብር) ሲሆን በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ከሆኑ ከአደራጃቸው አካል መደራጀታቸውንና በጨረታ ስራ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚጫረቱበትን ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን ያጠቃለለ እና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልቶ በታሸገ -ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል የቅዱስማርቆስ ቅድመ አንደኛ አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋ/ግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  9. ጨረታው በ11ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ላይ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቅዱስ ማርቆስቅ/አ/አ/መ ደረጃ ት/ቤት ላይበረሪ ይከፈታል።
  10. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸው እቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የማስያዝና የግዢ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።
  11. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ከሆኑ ካደራጃቸው አካል መደራጀታቸውን የጨረታ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  12. ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ ከጨረታው ያሰርዛል።
  13. መ/ቤቱ ጠቅላላ ለጨረታው ካቀረበው ብዛት 20% ከፍና ዝቅ ብሎ የግዢ ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል።
  14. ለጨረታው የተሰጠው ዋጋ ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
  15. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡- ፈረንሳይ ለጋሲዩን ንብ ባንክ አጠገብ ባለው ኮብልስቶን መንገድ ወደ ውስጥ 200 ሜትር ገባ ብሎ እንገኛለን።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡-011-154-8564 / 09-32-17-57-19/ 09-26 04 72 14 ደውለው መጠበቅ ይችላሉ ።

ቅዱስ ማርቆስ  ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-29
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 3፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-29 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: St.Markos Kindergarten & Elementary School
  • Buyer address: ፈረንሳይ ለጋሲዮን ንብ ባንክ አጠገብ ባለው ኮብልስቶን መንገድ ወደ ውስጥ 200 ሜትር ገባ ብሎ እንገኛለን።
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር በእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Oct 17, 2026)
  • Posted at: 2026-10-17T08:05:04.000Z
← Back to all tenders