Stationery

በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክፍለ ከተማ በወረዳ 7 ስር የሚገኘው የሜ/ጀ/ኃየሎም አርአያ የመጀ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክፍለ ከተማ በወረዳ 7 ስር የሚገኘው የሜ/ጀ/ኃየሎም አርአያ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ/ም የበጀት ዓመት የጨረታው መለያ ቁጥር 001

  • ሎት 1 አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 2,000
  • ሎት 2. አላቂ የትምህርት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 2,000
  • ሎት 3 የሰራተኞች የደንብ ልብሶች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 2,500
  • ሎት 4. አላቂ የፅዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 2,000
  • ሎት 5. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 3,000
  • ሎት 6. ቋሚ የቢሮ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 3,000
  • ሎት 8. ለህትመት ስራዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብርመጠን 2,000
  • ሎት 9. የተለያዩ መጻሕፍት የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 2,000

በዚህ መሰረት በጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፤ የዘመኑን ግብር አጠናቃችሁ የከፈላችሁ በመንግስት ግን አስ ኤጀንሲ ድህረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ የተመዘገቡ፤ የቫትና የቲን ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ።
  2. የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ በተረጋገጠ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ የምትችሉ
  3. ለጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሜ/ጀ ኃየሎም አርአያ የመጀ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ን/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት በግንባር በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የምትጫረቱትን እቃዎች ሳምፕል የሚቀርብባቸው ለሎት1 ለሎት2 ለሎት3 ለሎት 4 ለሎት5 ለሎት8 ለሎት9 ለሎቶቹ ናሙናውን ጨረታው ከመከፈቱ አንድ ቀን በፊት ሳንፕል በሚቀርብባቸው ሎቶች ላይ ያላቀረቡ ለጨረታ ውድድር አይቀርብም ማቅረብ (ማስገባት አለባቸው ጨረታው ከተከፈተ በኃላ በጨረታ የማናሳትፍ መሆኑን አንገልፃለን።
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
  6. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ስርዝ ድልዝ የሆነ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፋባቸውን ዕቃዎች በራሱ ባሸናፊው ትራንስፖርት ከነጉልበት ክፍያው ግዢ ፈፃሚው መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ግዴታ አለበት።
  8. ተጫራቾች የምታቀርቡትን ዋጋ ዝርዝር በሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በግልፅ ሞልታችሁ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውንና ኮፒ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ በስራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን በሜጄ ኃየሎም አርኢያ የመጀ ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ን/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 ማስገባት ይኖርባችኋል።
  9.  የጨረታ ሳጥኑ ማስታወቂያው ከወጣበት በ10ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሜጀ ኃየሎም አርኢያ የመጀ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡ 10ኛው ቀን የበዓል ቀን ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ማሳሰቢያ፡- በእስፔስፍኬሽን እና በዋጋ ማቅረቢያ ውጭ ሁለት ዋጋ መሙላት አይቻልም እንዲሁም በራስ በተሰጠው ሎት ፎርም ውጭ በእስክርቢቶ መሙላት እና ከታች አማራጭ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡ አድራሻ፡- ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አጠገብ ኖክ ማደያ ጎላ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ገባ ብሎ ስልክ ቁጥር፡- 011515-40-84 ወይም 0966 52-10-10 ፖስታ ሳጥን ቁጥር፡- 25993/1000

በል/ክ/ከ/አስ/ወረዳ 7 ት/ጽ/ቤት የሜ/ጀ/ኃየሎም አርአያ የመጀመሪያ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-28
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ሳጥኑ ማስታወቂያው ከወጣበት በ10ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-28 14:30
  • Bid opening (note): የጨረታ ሳጥኑ ማስታወቂያው ከወጣበት በ10ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Major General Hayelom Araya Primary School
  • Buyer address: ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አጠገብ ኖክ ማደያ ጎላ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ገባ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Lessan (Oct 17, 2026)
  • Posted at: 2026-10-17T08:24:12.000Z
← Back to all tenders