Stationery

የኮንሶ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ የጽህፈት መሣሪያ፣ አላቂና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ግዥ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ፣ የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ የሞተር ሣይክል ግዥ እና የሞተር መለዋዎጫ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ ቁጥር(ኮዞፋመ-ግጨ / ዕአግ/001-5ጨ/-2019 /

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የኮንሶ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ በ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት በመንግስት መደበኛ ገንዘብ እና ካፒታል ገንዘብ ምንጭ ከዞኑ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሰበሰበው የግዥ ዕቅድ ፍላጎት መሠረት፡-

  • የጽህፈት መሣሪያ፣
  • አላቂና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ግዥ፣
  • የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ፣
  • የፈርኒቸር ዕቃዎች እና
  • የሞተር ሣይክል ግዥ እና
  • ሞተር መለዋዎጫ ዕቃዎች ግዥን

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ በጥቅምት 1/2017 ዓ.ም ላይ አሻሽለዉ ያወጣው የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 71/2017 አንቀጽ 55 በንዑስ አንቀጽ 1፣2 እና 3 መሠረት በነዚህ ሥራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ እንዲሁም በመደበኛ ጨረታ ሠነዱ ላይ የተጠየቁትን መሠረታዊ ነጥቦች ወይም የህግ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ህጋዊ ግብር ከፋዮች አቅራቢዎችን ማህበራትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ጨረታውን ለመወዳደር የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች

በሙሉ፡-

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸዉ
  2. በዘርፉ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸዉ
  3. በዘርፉ /TI Number/የግብር ከፋይነት የምስክር ወርቀት ያላቸዉ
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
  5. በዘርፉ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወርቀት ያላቸዉ
  6. ማህበራት ከሆኑ ህጋዊ የሰዉነት ማረጋገጫ ምስክር ወርቀት ያላቸዉ
  7. ማህበራት መደራጀታቸውን የሚገልጽ ከአደራጅ መ/ቤት ህጋዊ የድጋፍ ዳብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  8. ተጫራቾች፡- የጨረታ ዝርዝር ወይም መደበኛ የጨረታ ሠነድ ይህ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ በኮንሶ ዞን ገቢዎች መምሪያ የሠነድ ሽያጭ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ 500/አምስት መቶ ብር /በመክፍል ገንዘብ የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ የዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁ. 11 በመቅረብ ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  9. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ ሠነድ የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ /CPO/ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ለጽ/መሣሪያ፣ አላቂና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ግዥ 20,000/ሃያ ሺህ ብር ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ 30,000/ሠላሳ ሽህ ብር/ ለፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ 30,000ሥሠላሳ ሽህ ብር/፣ የሞተር ሣይከል ግዥ 30,000ሥሠላሳ ሽህ ብር/ እና የሞተር ሣይክል መለዋዎጫ ዕቃዎች ግዥ 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ የቴከኒካል ኦርጅናል መረጃዎች ጋር በፖስታ አሽገዉ ለኮንሶ ዞን ፋይዳንና የነ ሩማት መጥሪያ ብሎ በአድራሻ በመፃፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በአንድ ኤንቬሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ቴክኒካልና ፋይናንሻል እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ኦርጅናልና 1ኮፒ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ጋር በትኅፊ በታሸገ በአንድ ኤንቨሎፕ ወይም የእናት ፖስታ ውስጥ በማስገባት በማሸም ማህተም በማሳረፍ፣ አድራሻ በመግለጽና በመፈረም ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  11.  ጨረታው የሚታሸገው በ16ኛው የሥራ ቀን ልክ 6፡00 ላይ ታሽጎ 8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ አከፋፈትን በተመለከተ የቴክኒካል ኦርጅናል ፖስታ በመጀመሪያ ደረጃ ይከፈታል፡፡ በጨረታ ማስታወቂያ መሠረት የተቀመጡ ቴክኒካል የግምገማ ከተገመገመ በኋላ ቀጥሎ የፋይናንሻል ኢንቨሎፕ /ፖ ስታ/ በመመሪያ መሠረት ተከፍቶ ይነበባል የተደረገዉ ወቂታዊ የገበያ ዋጋ ጥናት ጋር በማመሳከር ግምገማ የሚካሄድ ይሆናል።
  12. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ የማቅረብ የተከለከለ ነው።
  13. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን የውል ማስከበሪያ ሰነድን 10% በማስያዝ ባሸነፉበት የስራ የዉል ማስከበሪያና ተመጣጣኝ የቅድመ ክፍያ ዋስትና ይዘዉ ቀርበዉ 15 ስራ ቀናት ዉስጥ ውል ባይገባ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ውርስ ሆኖ በግዥ አዋጅና አፈፃፀም መመሪያ መሠረት ለጥፈተኝነት ሪፖርት ይቀርባል።
  14. ተጫራቾች ጨረታ በተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ ይዉላል፡፡ ጨረታዉ ይከፈታል በተባለዉ በ16ኛው ቀን በመንግስት የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  15. ተጫራቾች ተሟልተው ያለመገኘት የጨረታው አከፋፈት ሥነ-ሥርዓት ሊያስተጓጉል አይችልም።
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነ።
  17. ተጫራች የጨረታ ሠነድ ዋጋ ማቅረቢያ እንዲሁም ከመደበኛ የጨረታ ሠነድ በተጨማሪ ማስታወቂያ ጋር የተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ገዥ ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ፡-/09 06 48 25 47/09 16 14 00 71 /09 20 98 00 15 ደወለዉ ይጠየቁ

የኮንሶ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ -ካራት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-02
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ልክ 6፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-02 14:00
  • Bid opening (note): ይህ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ልክ 8፡00 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Konso Zone Finance Command
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Oct 17, 2026)
  • Posted at: 2026-10-17T08:38:52.000Z
← Back to all tenders