Equipment and Accessories
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ CCTV CAMERA ግዥ እና ገጠማ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር OSE/NCB/006/2019
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ CCTV CAMERA ግዥ እና ገጠማ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም አስፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
ተጫራቾች፡-
1. የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬት
2. የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት
4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No)
5. የአቅራቢነት ማስረጃ(Supplier list)
6. የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር ስለመወጣታቸው የሚገልጽ ማስረጃ፣ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸውጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ፡- ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ በመዋል በ16ኛው ቀን የሚዘጋ እና የሚከፈት ይሆናል፡፡ የጨረታ ሰነድ መግዣ ዋጋ ብር 200.00(ሁለት መቶ) መሆኑን እየገለጽን፣ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በፖስታ በማሸግ በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 2:30-8፡00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን።
የጨረታ ሳጥኑ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንተርፕራይዙ ዋና መ/ቤት ጎተራ አጎና ሲኒማ አጠገብ ባለኤር ህንፃ /Baleker Tower /4 ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 402 ይከፈታል።
ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢንተርፕራይዙ የሥራ ሰዓት፡- ከሰኞ-አርብ ጠዋት ከ2፡30-6፡30 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-11፡30 ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ፡- ስ.ቁ 011-416 03 09/ 011-466-25-27 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ
Tender details
- Deadline: 2026-11-02
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ በመዋል በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-02 14:30
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ በመዋል በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia Seed Enterprise
- Buyer address: ጎተራ አጎና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ህንፃ /Baleker Tower 4ኛ ፎቅ ላይ
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 17, 2026)
- Posted at: 2026-10-17T09:09:52.000Z