Equipment and Accessories
በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት የተለያዩ ኤሌክትሮድ እና የተለያዩ ዲስኮች በአገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- LP/OT/005/OKSF 1&3/2019
በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት የተለያዩ ኤሌክትሮድ እና የተለያዩ ዲስኮች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በአገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ/አዲስ የንግድ ፈቃድ ፣የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን /መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ/መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚመለከተው አድራሻ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00፣ ከሰዓት ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ ገዝተው በጫረታው መሳተፍ ይችላሉ።
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንደስትሪ ግሩፕ
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ
ግዥ ቡድን (ማስተባበር ቢሮ)
አድራሻ፡- ኮልፌ ቀራኒዮ፣
ከጦር ሃይሎች ወደ ዘነብ ወርቅ በሚወስደው መንገድ
በተለምዶ 3 ቁጥር ማዞርያ / ቶታል ገባ ብሎ
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ላይ
ሕ - B ቢሮ ቁጥር 1371/125 ፎቅ።
የስልክ ቁጥር (አድራሻ) +251-963442882/
+251913544731/+251-916170834
አዲስ አበባ
3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ህትመት የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡ በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው 17 /02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 17/02/2010 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
5. ጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው።
6. የጨረታው ማስረከቢያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ ለ 60 ቀናት ነው።
ፋብርካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-27
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-27 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Sugar Industry Group
- Buyer address: ካሳንቺስ ፣ ከንግድ ሚኒስቴር በስተቀኝ ገባ ብሎ ጆሴፍ ቲቶ መንገድ ከኪያሜድ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ሕንፃ በስተጀርባ የሚገኘው 4ኛ ፎቅ ላይ
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 17, 2026)
- Posted at: 2026-10-17T09:12:16.000Z