Equipment and Accessories

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያና በስሩ ለሚገኙ 9ኙም ፖሊስ መምሪያዎች ለ2019 በጀት ዓመት የስራ መገልገያ የሚሆን የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር L/K/S/C/P/D.../2019 ዓ.ም

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያና በስሩ ለሚገኙ 9ኙም ፖሊስ መምሪያዎች ለ2019 በጀት ዓመት የስራ መገልገያ የሚሆን የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድረን ግዥ መፈፀም በማስፈለጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታዉ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

ተ/ቁ

የሎት ዝርዝር

 

በሲ.ፒ.ኦ የሚያዝ የገንዘብ መጠን

1

በሎት 1.

የፅህፈት ዕቃዎች

20,000.00

2

በሎት 2.

የህትመት ውጤቶች

20,000.00

3

በሎት 3.

ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

20,000.00

4

በሎት 4.

የደንብ አልባሳት

15,000.00

5

በሎት 5.

የፅዳት ዕቃዎች

20,000.00

6

በሎት 6.

የግንባታ ዕቃዎች

20,000.00

7

በሎት 7.

የፈርኒቸር ውጤቶች

20,000.00

8

በሎት 8.

የህክምና መሳሪያዎች

25,000.00

9

በሎት 9.

የመኪና ጎማ ከመነዳሪዎች እና የትራፊክ ሞተር ሳይክል ጎማና መለዋዎጫዎች እንዲሁም የሲንግልና የደብል ፒካፕ ተሽከርካሪዎች የወንበር ልብስና የሙቀት መከላከያ

10,000.00

10

በሎት 10.

የፍሳሽ ቆሻሻ ወይም የመፀዳጃ ቤት መጣጭ እና የቀላል መኪና ማጓጓዣ ክሬን ኪራይ

15,000.00

1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው።

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

3. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።

4. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።

5. የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት

6. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ላይ ተቀባይነት የለውም።

7. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልግ ሁሉ በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በባንክ (ሲ ፒ ኦ) ብቻ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ በማሰራት ማምጣት አለባቸው።

8. የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት 45 ቀን ነው።

9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ግ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።

10. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዕቃ ናሙና ከጨረታው መክፈቻ ቀን በፊት ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከአያት አደባባይ ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ ባሮ ማደያ አጠገብ በሚገኘው መስሪያ ቤታችን 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 309 ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

11. በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ የማይመለስ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

12. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ እንዲሁም በ11ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

13. ጨረታው በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 505 ይከፈታል።

14. የጨረታው መክፈቻ ቀን ከስራ ቀናት ውጪና የከበረ በዓል ቀናት ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀናት ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዕት የሚከፈት ይሆናል።

15. ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

16. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116 391 021  በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-29
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋት 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-29 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋት 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Administration Police Commission
  • Buyer address: ኮልፌ ቀራዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ምሪያ ከጦርኃይሎች በስተግራ ቀለበት መንገድ ሲወርዱ የቀድሞው ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ሳይደርሱ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
  • Published on: Addis Zemen (Oct 17, 2026)
  • Posted at: 2026-10-17T09:15:32.000Z
← Back to all tenders