Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አቃቂ መንግሥት የመጀ/ደረጃ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም የሥራ ዘመን የተለያዩ ዕቃዎችን በ1ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አቃቂ መንግሥት የመጀ/ደረጃ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም የሥራ ዘመን የተለያዩ ዕቃዎችን በ1ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ፡-

  • ሎት 1 ደንብ ልብስ………..23,000.00
  • ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች…..5,000.00
  • ሎት 3 አላቂ የትም ዕቃዎች……15,001.00
  • ሎት 4 አላቂ የፅዳት ዕቃዎች…….5,014.00
  • ሎት 5 ልዩ ልዩ መሣሪያዎች……..1,851,00

የጨረታ ማስከበሪያ የግድ CPO ማሠራት አለበት፡፡ ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም።

1. የጨረታ ቁጥር 01/2019 ዓ.ም ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።

2. ተጫራቾች ላቅርቦቱ አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ሰርተፍኬት እና የታክስ ከፋይነት ቲን ነምበር ሊኖራቸው ይገባል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 ብር በመክፈል በእያንዳንዱ ሎት CPO በማስያዝ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30 ሰዓት እስከ 11፡30 ከግዥ ቢሮ ማግኘት ትችላላችሁ።

5. አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ መስጠት አይቻልም።

6. ተቋሙ ለሚገዛው ግዥ 20% ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል።

7. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን(ፋይናሻል) እና ፎቶ ኮፒውን(ቴክኒካል) ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮው ለዚህ ጨረታ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30–11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።

9. የሚቀርበው የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ የድርጅቱ ኃላፊ ስምና ፊርማ እንዲሁም አድራሻ እና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት።

10. አሸናፊ ተጫራች በሰነዱ ውስጥ በተመለከተው ጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም እስከ 7 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% CPO አስይዘው ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል።

11. መሥሪያ ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታ አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ ስድስት ወር ድረስ ውሉን ቢያድስም ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. በጨረታ ሰነድ ላይ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮች ካሉ የማብራሪያ ጥያቄ በፅሑፍ ከጨረታው መክፈቻ ሁለት ወይም ሦስት ቀናት በፊት ማቅረብ ይችላሉ።

13. አሸናፊው ድርጅት የግዥውን ውል ከፈረመበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ዕቃውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

14. የጨረታውን አካሄድ ለማዛባትም ሆነ ለማጭበርበር የሚሞክር ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይሆናል።

15. ማንኛውም ተጫራች ለሚያስገባቸው ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት።

16. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

17. ተጫራቾች የተጫረቱበትን ዕቃዎች ናሙና ወይም ሳምፕል ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች በምታቀርቡት ናሙና /ሳምፕል/ ላይ ምንም ዓይነት ስልክ ቁጥር እና ሌሎች ምልክቶች ማድረግ ከውድድር ውጪ ያደርጋል።

18. ከጥቃቅንና አነስተኛ ወይም ካደራጃቸው መሥሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው የሚጫረቱ ተጫራቾች ከሆኑ ምን አይነት ምርት እንደሚያመርቱ እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሀገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ /ጅምላ ንግድ/ ከሆነ ደግሞ ከአምራቹ የተሰጣቸውን ፈቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ካልሆነ ግን እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛትና የጨረታ ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0114 715 650 ይደውሉ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የአቃቂ መንግሥት የመጀ/ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-29
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-29 10:30
  • Bid opening (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Akaki Menegset Elementary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 17, 2026)
  • Posted at: 2026-10-17T09:20:29.000Z
← Back to all tenders