Stationery
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ወረዳ 06 ወይራ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesCleaning and Janitorial Equipment and Service
Addis Ababa
More tags
Textile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsPrinted Advertising MaterialsAdvertising and PromotionPrinting and PublishingOffice Machines and ComputersMaintenance and RepairOthersHouse and BuildingEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsOffice FurnitureFurniture and FurnishingComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesBuilding ConstructionConstruction and Water WorksFinishig WorksAmharic2merkatoWeira Primary School
Description
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው መለያ ቁጥር ወ/ት/ቤት /01/2019
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ወረዳ 06 ወይራ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
የግዢው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
|
ሎት 1 የጽህፈት እቃዎች |
30,000.00 (ሰላሳ ሺ ብር ብቻ) |
|
ሎት 2. የፅዳት እቃዎች |
20,000.00 (ሀያ ሺ ብር ብቻ) |
|
ሎት 3. የደንብ ልብስ |
30,000.00 (ሰላሳ ሺ ብር ብቻ) |
|
ሎት 4. የህትመት ስራ |
5,000.00 (አምስት ሺ ብር ብቻ) |
|
ሎት 5. ቋሚ እቃዎች |
20,000.00 (ሀያ ሺ ብር ብቻ) |
|
ሎት 6. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ስራ |
3,000.00 (ሶስት ሺ ብር ብቻ) |
|
ሎት 7. የግንባታ ጥገና ስራ |
30,000.00 (ሰላሳ ሺ ብር ብቻ) |
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ቅድመ ሁኔታዎችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ እንዲሁም የዘመኑን ግብር ከፍለው ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ፡፡
- በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ እና ያልታገዱ፡፡
- በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ እና የግብር ከፋይ መለያ (Tin) ቁጥር ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡዋአቸውን እቃዎች ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁና ለዚህም ለእያንዳንዱ እቃ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ለሎት o6 ከኮንስትራክሽን ባለስልጣን የተሰጠ ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም ከዚህ በፊት ለሰራቸው ስራዎች መልካም አፈፃፀም ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር) የስራ ተከታታይ ቀናት በስራ ሰዓት ቤቴል ወረዳ 06 አስተዳደር ገባ ብሎ የወይራ የመ/ደ/ት/ ቤት ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ የሰነዱን መግዣ ብር የአንድ ሎት መግዣ ዋጋ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ያላገናዘበ እጅግ የተጋነነ ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ የሚሰራውን ስራ ያላማከለ ከሆነ ተጫራቾች የዋጋ ትንታኔ (Cost breakdown) ከተገቢው መረጃ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል ፤ሆኖም የቀረበው ዋጋ ከስራው ጋር ያልተመጣጠነ (unbalanced rate) ከሆነ ተጫራቾች ከጨረታ ውድድር ወጪ ይደረጋሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙበት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቫትን ጨምሮ በግልፅ ዋናውንና ኮፒውን በመሙላት በታሸገ ፖስታ ከላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት 1ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የሰነዱን ኮፒና ኦሪጅናል ቴክኒካልና ፋይናንሻሉን በመለየት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ህጋዊ በሆነ ባንክ ሲፒኦ (CPO) ለወይራ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በማሰራት በየሎቱ በተጠቀሰው ዋጋ መሰረት በንግድ ዘርፋቸው ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣ በ11ኛው ቀን ይከፈታል ፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ላይ ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ይከፈታል፡፡
- መስሪያ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ የቅሬታ ጊዜ ማቅረቢያ ተከታታይ 07 (ሰባት) የስራ ቀናት መሆኑን አውቀው ቅሬታ ካላቸው በደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን የቅሬታ ጊዜ ካለፈ በኃላ በ(05) ቀን ውስጥ ውል በወቅቱ ቀርበው ካልተዋዋሉ የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ወደ ሁለተኛ ተጫራች የምናልፍ መሆኑን፡፡ እንዲሁም ውል ሲዋዋሉ ያሸነፉበት የእቃ 10 ፐርሰንት ሲፒኦ በማስያዝ በተጨማሪም እቃውን በ15 ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰአት 7፡30 እስከ 10፡00 1ኛ ፎቅ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ከስራ ቀናትና ከተጠቀሰው ሰዓት ውጪ ለሚፈጠረው መጉላላት ተጠያቂ የማንሆን መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች ናሙና በተጠየቀባቸው እቃዎች ጨረታው እስከ ሚዘጋበት እለት ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ጨረታው ከተዘጋ በኃላ የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ፀንቶ የሚቆየው 60 ቀን ይሆናል፤ከበጀት አንፃር ካሸነፈው ጨረታ 20% መጨመር ፣መቀነስ እንችላለን፡፡
- በጥቃቅንና አነስተኛ ላይ ተደራጅተው የሚሳተፉ አቅራቢዎች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ስትመጡ ካደራጃችሁ አካል በጽ/ቤቱ ሀላፊ ብቻ በስም እና በስራ ድርሻው የተፈረመ ቲተር ያለበት እና በእኛ አድራሻ የተፃፈ ደብዳቤ መሆን ይኖርበታል፤ ለሚመለከተው ሁሉ ተብሎ እንዲሁም በስኪርቢቶ የተፃፈ ደብዳቤ የማንቀበል መሆኑን አውቃችሁ አሞልታችሁ መምጣት ይኖርባችኃል፡፡ በተጨማሪም የምትወዳደሩበት ሎት መጠቀስ ይኖርበታል፤ በደፈናው የጨረታ ሰነድ እንዲወስዱ የሚል ደብዳቤ የማናስተናግድ መሆኑን አውቃቹ ደብዳቤው ላይ የምትወዳደሩበትን ሎት እንድትጠቅሱ፡፡
አድራሻ፡- በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ትምህርት ጽ/ቤት ወይራ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለበለጠ መረጃ፡- 0113-49-89-62/61/013-69-71-48
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ወረዳ 06 ወይራ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-30
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት
- Bid opening: 2026-10-30 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Weira Primary School
- Buyer address: በኮልፌ ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ወይራ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከወረዳ 06 ጽ/ቤት ዝቅ ብሎ የሚገኝ ነው፡፡
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Oct 18, 2026)
- Posted at: 2026-10-19T08:08:01.000Z
- Source: Qelal Tenders