House and Building Sale
የይዞታ ስፋት ጠቅላላ 236 ካ/ሜ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ወ/ሮ አብዮት ታደሰ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ህጻን ቃሉ በላይነህ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.183566 በቀን 16/02/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ መሰረት እና በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.193332 በቀን 24/3/2016 ዓ.ም ትዕዛዝ መሰረት ፍርድ ያረፈበት ቤት የካ/ክ/ከተማ ወረዳ 08 ውስጥ የሚገኝ የቤ.ቁ.515 ካርታ የለውም ሰነድ አልባ ነው ቤቱ ይዞታው ከቀበሌ ቤት ጋር በአንድ ግቢ ውስጥ ያለ ሲሆን የይዞታ ስፋት ከቀበሌ ቤት ጋር ጠቅላላ 236 ካ/ሜ ሲሆን የግለሰቡ ይዞታ ቤት ያረፈበት 13.48 ካ/ሜ ሲሆን ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው በጠቅላላው 171.19 ካ/ሜ የሆነ የሐራጅ መነሻ 5,960,508.26 (አምስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ስልሳ ሺህ አምስት መቶ ስምንት ከ26/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.193332 በቀን 04/06/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት እና በኮ/መ/ቁ.93332 በቀን 20/09/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ድጋሚ ሐራጅ 1/4ኛ 1,490,127.06 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ዘጠና ሺህ አንድ መቶ ሃያ ሰባት ከ06/100) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 9 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡ 30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ ቤት/ስም C.PO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በፌ/ ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ / ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-18
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-11-18 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Oct 18, 2026)
- Posted at: 2026-10-19T08:43:26.000Z
- Source: Qelal Tenders