House and Building Foreclosure

የቤቶች ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ትክክሏ ወልደየስ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ መገርሳ በዳዳ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/86951 በ10/12 ቀን 2004 ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/201443 በ24/4/2005 ዓ/ም በ18/10/2010 ዓ/ም በሐምሌ 14 ቀን 2015 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቀበሌ 10 ክልል በተጠሪ ስም የተሰራ በጋራዥ ድርጂት የመኪና ማቆሚያ ያለው G+3 ያለው (ግራውንድ ፕላስ ስሪ) የቤት ቁጥር አዲስ የሆነ ህንፃ በካ/ቁ//A000070701085 የተመዘገበ የሐራጅ መነሻ ዋጋ 67,887,100 (ስልሳ ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰማኒያ ሰባት ሺህ አንድ መቶ ብር) በካ/ቁ/ AA000070701050 የሐራጅ መነሻ ዋጋ 59,298,230.44 (ሀምሳ ዘጠኝ ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ስምንት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ብር 44/100) ጠቅላላ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 127,185,330.44 (አንድ መቶ ሀያ ሰባት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ሦስት መቶ ሰላሳ ብር 44/100) በካ/ቁ/AA000070701085 የተመዘገበው የቦታው ስፋት 1700 ካ/ሜ የቤቱ አይነት ለኢንዱስትሪ የህንፃው ወለል ከፍታ G+0 እና G+3 የሆነ በካ/ቁ/AA000070701050 የተመዘገበው የቦታው ስፋት 1,635 ካ/ሜ የቤቱ አይነት ለመኖሪያ የህንፃ ወለል ከፍታ G+0 ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል ሲሆን ካፒታል ጌን ግራ ቀኙ የሚከፍሉ መሆኑ ታውቆ ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

2ኛ በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ቀበሌ 09/43 የቤት ቁጥር 822 የሆነ ቤት ከነሰርቪሶች ና ማድቤት የሆነ ካርታ ያለው የቦታ ስፋት 500 ካ/ሜ የሆነ የሐራጅ መነሻ ዋጋ 20,294,650 (ሃያ ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና አራት ሺህ ስድስት መቶ ሀምሳ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል ካፒታል ጌን ግራ ቀኙ የሚከፍሉ መሆኑ ታውቆ ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ አፈ/ዳይሮክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልጻለን። 

 ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-19
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-11-19 12:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Oct 18, 2026)
  • Posted at: 2026-10-19T08:56:13.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders