Stationery
የዳግማዊምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesTextile, Garments and Uniforms
Addis Ababa
More tags
Textile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsPrinted Advertising MaterialsAdvertising and PromotionPrinting and PublishingCleaning and Janitorial Equipment and ServiceSpare Parts and Car Decoration MaterialsConstruction Machinery and EquipmentConstruction and Water WorksOthersMaintenance and RepairMachineryOffice Machines and ComputersWater Pipes and FittingsInstallation, Maintenance and Other Engineering ServicesElectrical, Electromechanical and ElectronicsEquipment and AccessoriesComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice FurnitureFurniture and FurnishingHouse FurnitureMedical Equipment and SuppliesHealth Care, Medical IndustryHealth Related Services and MaterialsBuilding and Finishing MaterialsHand Tools and Workshop EquipmentAmharic2merkatoMinilik II Health Science College
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት የአንደኛው ዙር ግልፅ ጨረታ፣
- ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያ ፣
- ሎት2. ደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፌት ፣
- ሎት 3 የህትመት ስራዎች፣
- ሎት 4 አላቂ የጽዳት ዕቃዎች ፣
- ሎት 5. የተሸከርካሪ ጌጣጌጥ እና ጥገና እቃዎች ፣
- ሎት 6 ለፕላንት ማሽነሪ እና ለመሳሪያ እድሳትና ጥገና ፣
- ሎት 7 ለቧንቧ እና ለኤሌክትሪክ ጠቅላላ ጥገና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች
- ሎት 8 ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን
- ሎት 9.ቋሚ የፈርኒቸር እቃዎች እና
- ሎት 10 ቋሚ የዲሞኒስትሬሽን(የህክምና) እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሟሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።
- በመስኩ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ የተሰጠ ማስረጃ እና የግብር መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከወሰዱት የጨረታ ሰነድ ዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ውጪ በሌላ ሞልቶ ቢያቀርቡ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ከፍለው መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል እና ፋይናንሽያሉን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት እሰከ ቀኑ 11፡00ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው፤ በ11ኛው ቀን እስከ አራት ሰአት ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው እለት ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ የግዥ ዳርክቶሬት ቢሮ የሚከፈት ሲሆን 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- በጨረታው ለመሳተፍ ከሎት 1 ፣ 2፣ 3፣ 4፣ 5 ፣ 6 እና 7 ላለው ለእያንዳንዱ ሎት 10,000.00 /አስር ሺ ብር/ ሎት 9 20,000(ሃያ ሺ) የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ሲኖርባቸው እና ሎት 8 እና 10. /50,000 ብር/ (ሃምሳ ሺ) ብር የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው ።
- ዘግይተው የቀረቡ የመወዳደሪያ ሠነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ የሚሆኑ ሲሆን ብር ወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል።
- በጨረታው ተወዳድሮ ያሸነፈውን እቃ በኮሌጁ ጥራት /ቴክኒክ ኮሚቴው) ጥራቱ ሲረጋገጥ ተጫራቹ በራሱ ትራንስፖርት ጭኖ በኮሌጁ ንብረት ከፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ያቀረቡት ዋጋ የሚቆይበት ጊዜ ቢያንስ ለ60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል ።
- ኮሌጁ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ የሚገዛውን እቃ ወይም አገልግሎት ብዛት መጠን እንደአስፈላጊነቱ እስከ 20 በመቶ ለመቀነስ ወይም ለመጨመር መብት ይኖረዋል።
- የዳ/ም/ህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ ወይም መረጃ ማግኘት ሲፈልጉ በስልክ ቁጥር 011 126-1653 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ ፡- ዳግማዊ ሚኒሊክ ኮፕሬሲቭ እስፕሻላይዝድ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው
የዳግማዊ ሚኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-10-30
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-30 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Minilik II Health Science College
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Oct 18, 2026)
- Posted at: 2026-10-19T10:03:27.000Z
- Source: Qelal Tenders