Equipment and Accessories
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችን ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and Accessories
Central Ethiopia
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችን ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 01 የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ግዥ
- ሎት 02 የጽሕፈት መሣሪያዎች ግዥ
- ሎት 03 የጽዳት ዕቃዎች ግዥ
- ሎት 04 የተሸከርካሪ / የመኪና /ዕቃ መለዋወጫ ግዥ
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያሳደሱ በግብር ከፋይነተ ተመዝግበው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበበትን የምዝገባ ወረቀት እንደዚሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር የዘመኑን የግብር ግዴታ የተወጡበትን መረጃ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ ቁጥር 01 በመቅረብ ለሥራው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ፋይናሻል እና ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው አሽገው ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / ለእያንዳንዱ ሎት ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ ወይም የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ያሽነፉባቸውን ዕቃዎች ወራቤ ከተማ ክልል ትምህርት ቢሮ ግዥና ንብረት አስ/ዳይሬክቶሬት ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን 8:00 ሰዓት ታሽጎ በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
- የውል ማስከበሪያ የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ7 ቀናት በኋላ ውሉን መፈረምና የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና አይነቶች ክፍያ በሚፈጸምበት የገንዘብ አይነት የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10% በውል ማስከበሪያነት ማስያዝ አለበት።
- ቢሮው ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታው ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በጨረታው ውድድሩ በአሸናፊው የተሰጠው ዋጋ ሳይቀይር እስከ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
- የጨረታ ሰነድ ፀንቶ የሚቆየው ለ45 ቀናት ብቻ ነው።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 046 771 0688 መጠየቅ ይችላሱ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክ/መንግሥት ትም/ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-10-28
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን 8:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-28 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን 8:30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Central Ethiopia Regional State Education Office
- Bid bond: 30,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 18, 2026)
- Posted at: 2026-10-19T11:08:13.000Z
- Source: Qelal Tenders