Stationery

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን መምሪያ የእንጅባራ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት እቃ አቅርቦቶችን ከውስጥ ገቢ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ


በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን መምሪያ በእንጅባራ ከተማ አስተዳደር የእንጅባራ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ለተቋማችን አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ እና
  •  ሎት 2. የጽዳት እቃ አቅርቦቶችን ከውስጥ ገቢ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4.  አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ የዋጋውን ጠቅላላ 10 በመቶ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለክታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ የጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት እቃ አይነቶችን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሆኖ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል እን/ጤ/አጠ/ጣቢያ ግ/ፋ/ቢሮ ቁጥር 35 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 15 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም እን/ጤ/አጠ/ጣቢያ ደረሰኝ በመሂ 1 ኮፒ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆነ በ2 ፖስታ ማለትም ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በእን/ከ/አስ/ጤ/አ/ጣቢያ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ይታሸጋል፡፡ ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በጤና ጣቢው ጨረታ ኮሚቴ የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈት ሲሆን፣ የመክፈቻ ቀኑ በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ግ/ፋ/ቡ ቢሮ ቁጥር 35 በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  11. አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ድምር ዋጋ ስለሆነ ተወዳዳሪዎች በመጫረቻ ሰነዱ የተዘረዘሩ ሁሉንም ዝርዝር መሙላት አለባቸው ወይም አንድ ተጫራችበአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የእቃ አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም፡፡ በዚሁ ምድብ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት መስፈርቱን በማሟላት ከጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ነው፡፡
  12. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሱ ወጭ እን/ከ/አስ/ጤ/አ ጣቢያ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
  13. መ/ቤቱ እንደ በጀት አቅሙ 20 በመቶ የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ተጫራቾች ያለምንም ሥርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ መሞላት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ላይኖረው ይችላል፡፡ በአጋጣሚ የተሰረዘ ከሆነ የተሞላውን ዋጋ የሞላው ድርጅት ከተሰረዘው ቦታ ባጠገቡ መፈረም አለበት፡፡
  16. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ እን/ጤ/አጠ/ጣቢያ ግ/ፋ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 35 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁርጥ 058 227 01 65 /09 12 33 37 94 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የእንጅባራ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-03
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-03 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: የእንጅባራ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ
  • Bid bond: 15%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Oct 19, 2026)
  • Posted at: 2026-10-19T13:28:30.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders