Equipment and Accessories

ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ እቃዎችን ግዥና ተከላ በጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል

Description

ጨረታና ጥሪ
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የውሃ ጉድጓድ ጠላቂ ፓምፕግዥ እና ተከላ ግልፅ ጨረታ Electric submersible pump

ኩባንያችን ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአማራ ክልል በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ በ124 ሄክታር ላይ በአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት የተሰማራ ኩባንያ ሲሆን ለእርሻ ልማቱ አገልግሎት የሚውል ሁለት የውሃ ጉድጓድ ጠላቂ ኤሌክትሪክ ሰመር ሰብል ፓምፕ, ኤሌክትሪክ ቦርድ ፣ኬብል፣ ፓይፕ እና ፊቲንግ እንዲሁም ተያያዥ እቃዎችን ግዥና ተከላ በጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።

 የፓምፑን አጠቃላይ ስፔሲፊኬሽን በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፤

የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ኩባንያው ተጫራቾችን ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. ህጋዊ የኤሌክትሮ መካኒካል ንግድ ፈቃድ ያለው እና በደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ ተቋራጭ የሆነ
  3. የኤሌክትሮ መካኒካል የድርጅቱን የብቃት ሰርተፊኬት ማያያዝ የሚችል
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው።
  5. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
  6. የተ. እ .ታ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል
  7. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያውን ሲፒኦ በጣና ፍሎራ ኃላ/የተ/የግ/ ማህበር ስም በተሰራ ሲፒኦ ለሚጫረትበት ግዥ ከተቀመጠው የመጫረቻ ዋጋ 2% ፐርሰንት ማስያዝ ይኖርበታ።
  9. የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ (ቅጹን) የማይመለስ ብር 500 በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከኩባያው ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 004 መውሰድ ይችላሉ።
  10. ተጫራቾች ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ጣና ፍሎራ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ በመገኘት የዋጋ ማቅረቢያ ቅጹን መውሰድ ይችላሉ።
  11. ጨረታው ከወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በባህር ዳር ጣና ፍሎራ ኃላ/የተ/ የግ/ማህበር ቢሮ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
  12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0918 481 598/0913 696 383 ወይም 058 2204 798 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
  13. በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ የዋጋና የሞዴል መረጃዎችን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን።
  14. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ ባህር ዳር ጣና ፍሎራ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ድረስ በመቅረብ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል።
  15. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 የተገለፁትን ማስረጃዎች አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  16.  ኩባንያው ውሉን እንደየአስፈላጊነቱ በየስድስት ወሩ ሊያድስ ይችላል።
    ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡-የዋና መስሪያ ቤት አድራሻ: ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 13 ሀይሌ ት/ቤት ጎን፣ ስልክ ቁጥር 0582204798 ኢሜል፡ [email protected] , [email protected] 
ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-11-05
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30
  • Bid opening: 2026-11-05 10:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Tana Flora P.L.C.
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 19, 2026)
  • Posted at: 2026-10-19T14:58:04.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders