House and Building Sale
የቦታ ስፋቱ በካርታ የተመዘገበ 312 ካ/ሜ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ወ/ሮ መሰሉ ገበረየስ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ወ/ሮ ፍቅርተ ገበረየስ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/196499 በ22/5/2017 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/202565 በ27/6/2017 ዓ/ም በ8/8/2017 ዓ/ም በ29/8/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 2 የቤት ቁጥር 400 የሆነ በተከሳሾች እና በከሳሽ አውራሽ በሟች ወ/ሮ ብዙወርቅ አየለ ስም ተመዘግቦ የሚገኝ ቤት የካርታ ቁጥር 38059 የቦታ ስፋቱ በካርታ የተመዘገበ 312 ካ/ሜ ሲሆን በልኬት በተረጋገጠው ላይ በመንገድ ጥናት ምክንያት ተቀንሶ 243 ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 9,438,482 (ዘጠኝ ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ ስምንት ሺህ አራት መቶ ሰማኒያ ሁለት ብር) ሆኖ የትራክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 4 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመ ቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.202565 በቀን 27/11/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በድጋሚ ሐራጅ ጨረታ ሆኖ 1/4ኛ ብር 2,359,620.50 ( ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሃያ ከ50/100) በማ ስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግ በው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ / ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-19
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-11-19 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Oct 19, 2026)
- Posted at: 2026-10-19T15:13:28.000Z
- Source: Qelal Tenders