Equipment and Accessories
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የተለያዩ የደንብ ልብስ ሎት እንድ የተለያዩ የቢሮ ጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች ሎት ሁለት የተለያዩ ህትመት ዓይነቶች /ሎት ሶስት የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች ሎት አራት የተለያዩ የአይቲ ዕቃዎች (ሎት አምስት / የተለያዩ የመኪና ዕቃዎች ሎት ሰድስት የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች (ሎት ሰባት/፤ የተለያዩ የህንፃ ቁሳቁስ መገጣጠሚያ ጥገና ዕቃዎች /ሎት ስምንት/ መስተንግዶ /ሎት ዘጠኝ/ እና የኮምፒተር፣ ፕሪንተር ፎቶ ኮፒ እና ጄኔሬተር ጥገና ባለሙያ ሎት አስር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው
1. ተጫራቾች በዘርፍ የንግድ ሥራ የተሠማሩበት ህጋዊ የዘመኑ ግብር የከፈሉበት ንግድ ፍቃድ ያላቸው በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት ያላቸው ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑንን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ የሚያቀርቡ፣ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሠርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
2. በአነስተኛ ጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ከአደራጀው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ሙሉ ቀን ጨምሮ ከጦር ኃይሎች በታች አጉስታ ድልድል በላይ ካልዲስ ኮፊ አጠገብ ባለው ነጭ ፎቅ ውስጥ በሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮልፌ ቀራኒዮ ከፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት 4ኛ ፎቅ ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሠነዱን በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ የቴክኒካል ሠነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ኤንቨሎፕ; እና የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ኤንቬሎፕ የድርጅቱ ስም ፣ አድራሻ ፣ ስልክ እና ማህተም እንዲሁም የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት ሎት በመፃፍ በየሎቱ በመለየት በታሸገ ኤንቬሎፕ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ በመቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5, ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ ብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.አር.PO/ ወይም የባንክ ዋስትና በጽ/ቤታችን ማለትም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት(Addis Ababa City Government Revenue Bureau Kolfe Keranyo Sub City Small Tax Payer Branch Office) ስም በማስያዝ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከ 9 /2/2019 አስከ 19/2/2019 ዓ/ም 11፡15 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
6. ተጫራቾች ለሚወዳሩበት ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው። የሚቀርበው የመወዳደሪያ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፣ የፎቶ ኮፒ ቀለምና የፕሪንተር ቀለም የምትጫረቱ የዋስትና ደብዳቤ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
7. የጨረታ ሣጥኑ በ22/2/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤታችን የግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ክፍል ውስጥ ይከፈታል።
8. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
9. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
10. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ ዋጋ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት መስፈርቶች ውጭ በሰነዱ ላይ ባለው መመሪያ ተፈፃሚ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ በስልክቁጥር 011 369 0856/ 011 383 6636 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-29
- Bid closing time: 17:15
- Bid opening: 2026-11-01 09:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kolfe Keranio Sub City Small Tax Payers Branch Office
- Bid bond: 5000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 19, 2026)
- Posted at: 2026-10-19T15:23:22.000Z
- Source: Qelal Tenders