Tri Wheeler, Motorcycles and Bicycles Purchase

የጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ፣

የጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት 

  1. የኤሌክትሪክ ሞተር ሣይክል
  2. ፈርኒቸር 
  3. የሞተር ሣይክል ጐማ 
  4. የግንባታ ዕቃዎች 
  5. ሕትመት
  6. ናይትሮጅን ጃር 
  7. የኖራ ውህድ ከነትራንስፖርት
  8. የእንስሣት መድኃኒትና የሕክምና መገልገያ 
  9. የፖሊቲን ቲውብ/ ፕላስቲክ ባግ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና በአቅራቢት የተመዘገቡ
  4. የንግድ ፍቃድና ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  5. የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
  6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-5 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 15 ባሉት ቀናት ብር 300.00/ ሦስት መቶ ብር/ በጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የባንክ ሂሣብ ቁጥር 1000038613263 በማስ ገባት እና የባንክ አድቫይስ ይዘው ከጋሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ ደረሰኙን በማሳየት ከጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ(BiD security) ለእያንዳንዱ 80,000/ሰማኒያ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በዋናው የሕጋዊነት ሰነድ እንቬ ሎፕ ውስጥ አስገብተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በማዘጋጀት በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ የሚወዳደሩበ ትን ዓይነት በፖስታው ላይ በመለየት በግዥና ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው ሣጥን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን እስከ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስ ገባት ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው ከወጣበት እስከ 16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል።
  11.  ማንኛውም ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ ያለተጨማሪ ወጪ እስከ ቢሮአችን በማምጣት የማስ ረከብ ኃላፊነት አለበት።
  12. የጨረታ መክፈቻ በበዓላት ወይም በሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  13.  መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተ ጠበቀ ነው።
  14.  ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር- 046-881-3338 በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጋሞ ዞን
ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
አ/ምንጭ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-03
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት እስከ 16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-03 10:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት እስከ 16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Gamo Zone Finance Department
  • Bid bond: 80,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 19, 2026)
  • Posted at: 2026-10-19T15:31:23.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders