Stationery
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡባዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የጽሕፈት መሳሪያዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር እና የወለል ምንጣፍ ግዥ በጨረታ ዋጋ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የቢሮ መገልገያ ዕቃ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት የቢሮ መገልገያ ዕቃ ማለትም
- ሎት 1 የጽሕፈት መሳሪያዎችን
- ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ
- ሎት 3 ፈርኒቸር እና
- ሎት 4 የወለል ምንጣፍ ግዥ በጨረታ ዋጋ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ስለዚህ ተጫራቾች –
- አግባብነት ያለው ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው እና የዘመኑን ወይም 2019 ዓ.ም ግብር የገበሩበት ማረጋገጫ ያለው/ያላት አሪጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
- የ2018 ዓ.ም የግብር ክሊራንስ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል የምትችል።
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ እና በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
- ጊዜው ያላለፈበት በአቅራቢነት በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከመንግስት መ/ቤት የተሠጠ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል።
- የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 30,000 ከታወቀ ባንክ /CPO/ማስያዝ የሚችል።
- የውል አፈፃፀም ዋስትና ማስከበሪያ ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 10% በጥሬ ወይም ከታወቀ ባንክ የተሰጠ CPO/ማስያዝ የሚችል።
- ማንኛውንም ወጪዎች ማለትም የጉምሩክ የትራንስፖርት የባንክ እና የሌሎች አገልግሎት ወጪዎችን በራሱ ሸፍኖ ዕቃውን ማስረከብ የሚችል
- ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የዕቃዉን ዝርዝር ወይም ስፔስፍኬሽን በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ መመልከት ይችላሉ።
- በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ያቀረቡት ናሙና ወዲያው ተመላሽ ይደረጋል።
- ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400/አራት መቶ ብር/ በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በመክፈል እና ሰነዱን በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ግዥ ሥራ ሂደት ቢሮ በመውሰድ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነዱ ላይ የአንዱን ዋጋ ብቻ ቨትን አካቶ በመሠላት ቴክኒካል ዶክመንት እና ፋይናንሻል ኦርጅናል እንዲሁም ሁለት ሁለት ፎቶ ኮፒው ለየብቻ በማድረግ በአንድ ፖስታ አሽጎ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ግቢ ውስጥ ባለው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሳጥን በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒና ማመልከቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መምሪያው በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ሌላው ተጫራች ተንተርሶ መጫረት አይችልም።
- የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ጨረታው መክፈቻ በሥራ ቀን ካልዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይሆናል።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-10-29
- Bid closing time: 14:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-29 15:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: ደቡባዊ ሲዳማ ዞን ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት
- Bid bond: 30,000.00 ብር
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 19, 2026)
- Posted at: 2026-10-19T15:43:35.000Z
- Source: Qelal Tenders