Finishig Works

ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር በ10ኛ ወለል በንፋስ ስልክ ቀለም የመቀባት ሥራ አጠቃላይ የቀለም፣ የማትሪያል እና የእጅ ዋጋ ጨምሮ ለብቻ ወይም የእጅ ዋጋ ብቻ እንዲሁም የአልሙንየም ፓርቲሽን ሥራ በካሬ ዋጋ በማቅረብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

ቁጥር፡ ይሓ/15864/19

የቀለም መቀባት እና የአልሙንየም ፓርቲሽን ሥራ ለማሰራት የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር በ10ኛ ወለል በንፋስ ስልክ ቀለም የመቀባት ሥራ አጠቃላይ የቀለም፣ የማትሪያል እና የእጅ ዋጋ ጨምሮ ለብቻ ወይም የእጅ ዋጋ ብቻ እንዲሁም የአልሙንየም ፓርቲሽን ሥራ በካሬ ዋጋ በማቅረብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ ተጫራቾች ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7 /ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

በዚሁ መሰረት

  1. ተጫራቾች በይሓ ሲቲ ሴንተር ሰው ሃብት አስተዳደር መምሪያ ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ የሚሰራው ሥራ በማየት መጫረት እና ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ።
  2. ተጫራች የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  3. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቀለም ሥራ የሚጫረቱ ብር 5,000(አምስት ሺ ብር) እና ለአልሙንየም ፓርቲሽን ሥራ ለሚጫረቱ ብር 10,000(አስር ሺ ብር) በይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ሥም ሲፒኦ (CPO) በማሰራት ማስያዝ ይኖርበታል።
  4. ተጫራች ከዚህ በፊት በጨረታ የተሳተፈባቸው ድርጅቶች(መ/ቤቶች) የመልካም የሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  5. ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት በዕለቱ ጥቅምት 16/02/2019 በስራ ሰዓት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይሆናል።
  6. ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በዕለቱ ጥቅምት 16/02/2019 በስራ ሰዓት ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ይሆናል።
  7. ተጫራች በጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ 2ኛ ፎቅ ሰው ሃይል አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ ውል ማሰር ይኖርበታል፡፡
  8. ተጫራች በጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ 2ኛ ፎቅ ሰው ሃይል አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ ውል ተዋውሎ ወደ ስራው ካልገባ ለጨረታ ማስከበሪያ ለቀለም ሥራ ለመሥራት ለተጫረቱ ብር 5,000(አምስት ሺ ብር) እና ለአልሙንየም ፓርቲሽን ሥራ ለመሥራት ለተጫረቱ ብር 10,000(አስር ሺ ብር) ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ወደ ይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ሒሳብ ቁጥር ገቢ ይሆናል፡፡
  9. ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ መገኘት ይችላሉ።

አድራሻ፡– አዲስ አበባ ስቴድየም ቤተ ዛታ ሆስፒታል ፊት ለፊት ‹‹ይሓ ሲቲ ሴንተር›› ህንጻ 2ኛ ፎቅ ስልክ ቁጥር-
የቢሮ 011558012 /0115576954/ ሞባይል – 0922079575
ማሳሰቢያ፡– ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 


Tender details

  • Deadline: 2026-10-26
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid opening: 2026-10-26 15:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yiha Real Estate P.L.C.
  • Buyer's registered address: ይሓ ሲቲ ሴንተር ህንፃ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published on: Reporter (Oct 18, 2026)
  • Posted at: 2026-10-20T06:56:26.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders