Vehicle and Machinery Sale

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ተሽከርካሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን እና በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከቱትን ተሽከርካሪዎች በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 ለባንች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ተሽከርካሪዎቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
  • ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀን እና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።
  • ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
  • በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
  • የጨረታ ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 7 ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ B 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር እና ዴት ሊቲጌሽን ዲቪዥን የጨረታ ክፍል ውስጥ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 15 11 53 እና 0115 15 07 11 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡
  • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ተ.ቁ

 

የተበዳሪው ስም

 

የመያዣ

 ሰጪ ስም

 

የሰሌዳ ቁጥር

 

የተሸከርካሪው ዓይነት እና የተሰራበት ዘመን

 

የተሸከርካሪው ሞዴል

 

የሻንሲ ቁጥር

 

የሞተር ቁጥር

 

የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር

 

ጨረታዉ

የሚካሄድበት ቀን

 

የምዝገባ ሰዓት

 

የጨረታ

ሰዓት

 

1

አቶ አየነዉ ገዛቸዉ አድማሴ

 

ተበዳሪው

 

ኢት- 03-A16386

 

የጭነት፣ 2021

 

ZZ1167G 4715C1

 

LZZ5BBFF3 ME922519

 

YC4E 160.33 E371 7M00381

 

6,200,000.00

 

ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም

 

4:30- 5:30

 

5:30- 6:00

 

 


Tender details

  • Deadline: 2026-11-03
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-11-03 12:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
  • Buyer's registered address: Addis Ababa Ethiopia
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Reporter (Oct 18, 2026)
  • Posted at: 2026-10-20T07:32:56.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders