Stationery

ለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የተለያዩ እቃዎች ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ (NCB 001/2019)

ለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የተለያዩ እቃዎች ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ።

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊና የዘመኑ ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የተመዘገቡበት የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስራ አራት ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ስድስት ኪሎ ከመርሃ ዕውራን ማህበር ዝቅ ብሎ ከበላይ ዘለቀ ትምህርት ቤት ፊትለፊት በሚገኘው ለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የበጐ አድራጎት ድርጅት ዲን ኦፊስ ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ መሠረት በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ በለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የበጐ አድራጎት ድርጅት ስም ሞልተው ከኦሪጅናል የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተ.ቁ

 

የግዥው ዓይነት

 

የጨረታው መለያ ቁጥር

 

የጨረታ ማስከበሪያ (በብር)

 

የጨረታው መዝጊያ

 

የጨረታው መክፈቻ

 

ቀን

 

ሰዓት

 

ቀን

 

ሰዓት

 

1

የጽሕፈት መሣሪያዎች ሎት 1

 

NCB 001/2019

 

3,000.00

በ15ኛው ቀን

4፡30

በ15ኛው ቀን

4:45

2

የጽዳት አገልግሎት እቃዎች

ሎት 2

 

NCB 001/2019

 

3,000.00

በ15ኛው ቀን

4፡30

በ15ኛው ቀን

4:45

3

ጥራጥሬና ሸቀጣሸቀጦች ሎት 3

 

NCB 001/2019

 

3,000.00

በ15ኛው ቀን

4፡30

በ15ኛው ቀን

4:45

4

የህክምና እቃዎች ሎት 4

 

NCB 001/2019

 

3,000.00

በ15ኛው ቀን

4፡30

በ15ኛው ቀን

4:45

5

ኮምፈርት ሎት 5

 

NCB 001/2019

 

3,000.00

በ15ኛው ቀን

4፡30

በ15ኛው ቀን

4:45

6

የተማሪዎች ዩኒፎርም

 

NCB 001/2019

 

3,000.00

በ15ኛው ቀን

4፡30

በ15ኛው ቀን

4:45

4. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የመወዳደሪያ ሰነዶች ቴክኒካል ኒካል አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሺያል አንድ ኦሪጅ እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሺያል አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ ለየብቻው አሽገው የጨረታውን ስምና ቁጥር በመፃፍ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ተከታታይ ቀን ጀምሮ በሰንጠረዡ መሠረት በኮሌጁ ዲን ኦፊስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም። 

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ስድስት ኪሎ ከመርሃ ዕውራን ማህበር ዝቅ ብሎ በበላይ ዘለቀ ትምህርት ቤት ፊትለፊት በሚገኘው ለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የበጐ አድራጎት ድርጅት ዲን ኦፊስ ውስጥ ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።

6. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታዎች ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚያገኙ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0955-11-11-11 ደውለው ወይም በአካል መጠየቅ ይችላሉ።

7. ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የበጎ አድራጎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-03
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 4፡30
  • Bid opening: 2026-11-03 10:45
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 4፡45
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: LE DEG MIDWIFERY COLLEGE
  • Bid bond: 3,000.00 ብር በየሎቱ
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት 300.00 /ሶስት መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Oct 20, 2026)
  • Posted at: 2026-10-20T12:15:32.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders