Stationery

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት ለፖሊስ ኮሚሽን የተለያዩ ክፍሎች እና ቢሮዎች አገልግሎት የሚወል የጽህፈት መሳሪያዎች እና የጽዳት እቃዎች ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት ለፖሊስ ኮሚሽን የተለያዩ ክፍሎች እና ቢሮዎች አገልግሎት የሚወል የጽህፈት መሳሪያዎች እና የጽዳት እቃዎች ግዢ ለመፈጸም ጨረታ ለማውጣት ስለምንፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል ፡፡

  • የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ለ15 ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት የሥራ ሒደት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፤ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ከፋይ የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ ፣ተጨማሪ እሴት ታክስ ፤ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆንና የጨረታው ውጤት እንደታወቀ የሚመለስ የሚጫረቱበት፤

  • ለጽህፈት መሳሪያዎች ብር 70,000.00/ሰባ ሺ ብር/
  • ለጽዳት እቃዎች ግዢ ብር 40,000.00/አርባ ሺ ብር/በባንክ በተረጋገጠ CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ተመራጭነት አለው፡፡ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለየብቻ በፖስታ በማሸግ በአንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሰነድ ጥቅምት 10/209 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም 1፡00 ሰዓት በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን በፋይናንስና ግዢ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡

ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 25/2019.ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሣጥኑ ታሽጎ 3፡30 ሠዓት ይከፈታል፡፡ ፖሊስ ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0251-11-74-55/0251-11-37-43ፖ.ሣ.ቁጥር 1453 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-11-04
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid opening: 2026-11-04 09:30
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Dire Dawa Administration Police Commission
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 20, 2026)
  • Posted at: 2026-10-20T12:59:48.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders