Equipment and Accessories
የአዳማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማዉ መስተዳድር ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒከስ እቃዎችን ለመግዛት በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and Accessories
Oromia
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማዉ መስተዳድር ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒከስ እቃዎችን ለመግዛት በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለዉ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉና፤ የዘመኑን ግብር ከፍሎ ማጠናቀቁንና፤ጨረታ ላይ እንዲሳተፍ የሚል ማስረጃ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ጽ/ቤት ማቅረብ አለበት።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT ) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጽ/ቤቱ ስም ሲንቄ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1054551161211 ላይ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት በጽ/ቤቱ የግዢ የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN No.) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸዉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ፎቶ ከፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ለእያንዳንዱ ጨረታ ማስከበሪያ CPO ብር 50,000.00(ሀምሳ ሺህ ብር) ሲሆን ለጥቃቅን ና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ የትኛውንም የዋስትና ደብዳቤ የማንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።
- ተጫራቾች ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ለየብቻ ኦርጂናል እና ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ አለበት። ቴክኒካሉን ያለፉት ተወዳዳሪዎች ፋይናንሻላቸው ይከፈታል።
- ጨረታው የሚከፈተው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ 16ኛዉ ቀን የስራ ቀን ከሆነ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛዉ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በአዳማ ከተማ ገንዘብ/ፅ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ግዢ ክፍል ውስጥ ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም መ/ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰዉ ሰዓት ጨረታዉ ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ ዕቃዎቹን እስከ አዳማ ከተማ ገንዘብ ፅ/ቤት መጋዘን ድረስ በራሱ ወጪ አጓጉዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ በተሰጠዉ መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በውስጥ ማስታወቂያ ና በስልክ እንደተገለፀ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ከአዳማ ከተማ ገንዘብ ፅ/ቤት ጋር መፈራረም አለበት። ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ገቢ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች ለውድድር የሚቀርበው ቫት ተጠቃሚ ሲሆን ፣ 7.5 % በክፍያ ጊዜ የሚቀነስ ይሆናል።
- መስሪያ ቤቱ ከሚያደርገዉ የግዢ ውል 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ መገንዘብ አለበት።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09-73-33-45-15 በስራ ሰዓት ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።
የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-06
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን የስራ ቀን ከሆነ በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-06 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን የስራ ቀን ከሆነ በ4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Adama City Administration FEDB
- Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Oct 20, 2026)
- Posted at: 2026-10-20T13:31:08.000Z
- Source: Qelal Tenders