Equipment and Accessories

የደቡ/ምዕ/ኢት/ሕ/ክል/መ/ጠቅ/ፍ/ቤት አይሲቲ እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ጽ/መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ምንጣፍና መጋረጃ እና ፈርኒቸር በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የደቡ/ምዕ/ኢት/ሕ/ክል/መ/ጠቅ/ፍ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለፍ/ቤቱ ሥራ አገ/ት ዕቃዎችን በተለያዩ  ሎት ከህጋዊ አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 አይሲቲ እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣
  • ሎት 2 ጽ/መሣሪያዎች ፣
  • ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች፣
  • ሎት 4 ምንጣፍና መጋረጃ፣
  • ሎት 5 ፈርኒቸር

በዚሁ መሠረት ከተጫራቾች ተሟልቶ መቅረብ ያለበት

  1. በሥራ መስኩ ሕጋዊ እና የዘመኑ ግብር ተከፍሎ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት
  2. የቲን ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
  3. በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችል
  4. አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በተጠቀሰው ስፔስፍኬሽን መሠረት በማሟላት በራሱ ትራንስፖርት ድርጅቱ ወደሚያዘጋጀው እስቶር ለማቅረብ የሚችሉ
  5. በጨረታው የሚሳተፍ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በደቡብ ምዕ/ኢ/ህ/ክ/ገቢዎች ቢሮ አካውንት ቁጥር 1000513995777 ላይ በማስገባትና የገቢ ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከጠቅላይ ፍ/ቤቱ ግዥ ፋይ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት መውሰድ የሚችሉ።
  6. የጨረታው አየር ላይ የቆይታ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታው ሳጥን በ 16ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ 5፡00 ሰዓት የሚከፈት ሆኖ የመክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ባይሆን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  7. የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት የተለያዬ ሲሆን ሎት 1 50,000.00/ሀምሳ ሽህ ብር/ ከሎት 2 እስከ ሎት 5 ላሉት ለእያንዳንዳቸው 5000.00/አምስት ሽህ ብር/ ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።
  8. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ለእያንዳንዱ ዕቃ ግልፅ የሆነ ቴክኒካል መግለጫ ማቅረብ አለባቸው።
  9. ተጫራቾች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የመጫረቻ ሰነድ ሰንጠረዥ ላይ /በድርጅቱ ፕሮፎርማ ማቅረቢያ ከሆነ በመ/ቤቱ የተዘጋጀው ቅደም ተከተል ሳይዛባ / ዋጋ በመሙላት በአንድ ኮፒ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ በታሸገ ፖስታ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን የጨረታው ቀንና ሰዓት ከማለቁ በፊት ማስገባት ይጠበቅባቸዋ።
  10. የሚከፈትበት ቦታ በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ግዥ ክፍያ ዳይሬክቶሬት ቢሮ አንደኛ ፎቅ ላይ ነው።
  11. ተጫራቾች የተፈለገውን የእቃ ጥራት ወይም ብዛት አሟልቶ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
  12.  የተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎች ያለመገኘት የጨረታውን መከፈት ሂደት አያስተጓጉልም።
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 047 135 1716

የደቡ/ ምዕ/ ኢት/ ሕ/ክል/ መ/ ጠቅ/ ፍ/ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-04
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-04 11:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ5፡00 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 20, 2026)
  • Posted at: 2026-10-20T13:38:38.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders