Equipment and Accessories
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት ፋብሪክ ሲንግል ሀመር ከራሸር ስፔር ፓርት (Single Hammer Crusher Spare Parts) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የሀገር ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ሙሲፋ/07/2019
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት ፋብሪክ ሲንግል ሀመር ከራሸር ስፔር ፓርት (Single Hammer Crusher Spare Parts) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው (የ2018/2019 ዓ.ም)፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 (አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር) ከነቫቱ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ገርጂ አካባቢ የቀድሞው ኢምፔሪያል ሆቴል መዳረሻ ወለል ከሚገኘው የፋብሪካው ግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.PO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዕለቱ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል። ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ /አዲስ አበባ/
Tender details
- Deadline: 2026-11-03
- Bid closing time: 09:30
- Bid opening: 2026-11-03 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Mugher Cement Factory
- Buyer's registered address: Addis Ababa, Ethiopia
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 575.00 (አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 20, 2026)
- Posted at: 2026-10-20T14:26:03.000Z
- Source: Qelal Tenders