Stationery

የአ.አ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ቃሊቲ አዲስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ቋሚ እቃ፣ የጽዳት እቃዎች እና የመኪና ጎማ እና ጌጣጌጦች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የቃሊቲ አዲስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2019ዓ.ም ለፅ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን ማለትም፣

  • ሎት 1. አላቂ የቢሮ እቃዎች 
  • ሎት 2. ቋሚ እቃ
  • ሎት 3. የጽዳት እቃዎች
  • ሎት 4 የመኪና ጎማ እና ጌጣጌጦች

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች በመስኩ የተሰማሩ፣ህጋዊ ና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የኢፌዴሪ የገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የተ.እ.ታ ተመዝጋቢዎች ለመሆናቸው ኮፒ ማስረጃ እና Tin No ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
  2.  ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  3.  ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ/Financial |ሰነድ ፣እንዲሁም አስፈላጊ ቴክኒካል ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በመለየት ኦርጂናልና ኮፒውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ግዥ ክፍል በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 /አምስት ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን መ/ቤቱ በሰጣቸው ሰነድ ላይ መሙላት እና በእያንዳንዱ የመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ፊርማ በመፈረም የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና እንዲቀርብ ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ጨረታ ከመከፈቻ ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፣በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
  8. ተጫራቾች ውሉን ሲዋዋሉ ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  9.  መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0904159873/0913149064 ደውሎ

መጠየቅ ወይም ቃሊቲ

ማሰልጠኛ ግቢ የአሸከርካሪና ተሸከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ቃሊቲ አዲስ ቅ/ጽ/

ቤታችን ፋይናንስ ክፍል በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአ.አ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፍቃድና

ቁጥጥር ባለስልጣን ቃሊቲ አዲስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-31
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-31 11:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Driver and Vehicle Licensing Control Authority Kaliti Addis Branch Office
  • Bid bond: 5000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 20, 2026)
  • Posted at: 2026-10-20T14:28:16.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders