Stationery

የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የጽህፈት መሣሪያና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር WWC 04/2019

የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

  • የጽህፈት መሣሪያና
  • የጽዳት ዕቃዎች ግዥ

የተጫራቾች መመሪያ የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመታዊ የጽህፈት መሣሪያና የጽዳት ዕቃዎች መግዛት ስለፈለገ ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ በጨረታ ቁጥር WWC 04/2019 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።

  1.  የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TI፤የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት።ተጫራቾች እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በጀርባው ፊርማና ማህተም በማድረግ በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል።
  2.  ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ለ60 ቀን እና ከዚያ በላይ ጸንቶ የሚቆይ በኮርፖሬሽናችን ስም የተሰራ የከፍያ ትእዛዝ የተረጋገጠ.ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (unconditional Bid bond guarantee/ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ/ ብር ማስያዝ አለባቸው። አሸናፊው ድርጅት ከተለየና ውል ከተፈረመ በኋላ ላላሸነፉ ድርጅቶች የጨረታ ማስከበሪያ ይመለስላቸዋል።
  3. ተጫራቾች የሚሰጡትን ዋጋ በተናጠል የምናወዳድር ይሆናል የሚሞላው ዋጋ ማንኛውንም ወጪ ያካተተ ይሆናል።
  4. ጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) ባሕርዳር ከተማ ከሚገኘው ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 10 ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን በተናጠል ለየብቻ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የጋዜጣ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ባህርዳር ከተማ ከሚገኘው ውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ግዥና አቅርቦት ከፍል ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ አይቻልም ካለ ግን ዋጋውን በሞላው አካል መፈረም ይኖርበታል።በሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ላይ ህጋዊ የድርጅቱ ተወካይ ስም ፊርማ እና ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል።
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ግዥና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 25 ጨረታው ወጥቶ በአየር ላይ ከቆየበት የመጨረሻ ቀን ማለትም በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት ይከፈታል የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም፡፡
  8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።ይህንንም በሚያደርግበት ጊዜ በኮርፖሬሽኑ የማስታወቂያ መለጠፊያ ቦርድ ማስታወቂያ ይገለፃል።
  9. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ግዥና አቅርቦት ዳይሬክትሬት ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል።

ለበለ ጠመረጃ፡-የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት

ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 መሰናዶ ት/ቤት ጎን

ውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ፖ.ሣ.ቁ 106

ስልክ ቁጥር 058 222 1479/09-30-11-17-46

ባህር ዳር

የውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-11-09
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-09 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Water Works Corporation
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 1,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 20, 2026)
  • Posted at: 2026-10-20T14:32:04.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders