Equipment and Accessories

ውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ የዕቃ አቅርቦት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር NCB WWC 05/2019

የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ዋናው መ/ቤት) ለጋራዥ እና ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የዕቃ አቅርቦት ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ በጨረታ ቁጥር NCB WWC 05/2019 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።

ተቁ

የሎት ቁጥር

ዋና ዋና የዕቃ ዝርዝር/ዓይነት

Summery of goods

መለኪያ

 

ብዛት

 

ምርመራ

1

ሎት-1

Difference types of Welding machine

በቁጥር

 

02

 

2

ሎት-2

Difference types of Electrical materials

በቁጥር  /ሴት/ሜትር

ጥቅል

 

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።

  1.  የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/፤የቫት ምዝገባ የምስከር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት።ተጫራቾች እነዚህንና ልሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በጀርባው ፊርማና ማህተም በማድረግ በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚሆን ለ88 ቀን እና ከዚያ በላይ ጸንቶ የሚቆይ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ለሎት 1 ብር 50,000.00 / ሃምሳ ሺህ ብር/፣ለሎት 2 150,000.00/አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ሲ.ፒ. ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማሰራት ማስያዝ አለባቸው።
  3. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20 /ሃያ ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ በውሀ ስራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ከኮርፖሬሽኑ ዋና ግቢ ከጠቅላላ ሒሳብ ክፍል ቢሮ እና አዲስ አበባ ከሚገኘው ከአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሳሪስ ቦንጋ ሆቴል ገባ ብሎ 100 ሜትር በመሄድ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች መወዳደሪያ ሀሳባቸውን ማለትም የቴከኒክና የዋጋ ሰነዳቸውን በሁለት ቅጅዎች ዋናና ቅጅ በማለት ቴክኒካልና ፋይናንሻል በተናጠል ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. የቴክኒካል ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ግቢ ግዥና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20 ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
  6. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  7. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ግዥ እና አቅርቦት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቁጥር 25 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቀጥር– ዐ58222-14 79 መጠየቅ ይቻላሉ።
  8. ማሳሰቢያ፤- አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የጨረታ ሰነድ መግዛት ብቻ እንጂ የጨረታ ፖስታውን ማስገባት የሚቻለው

ባህርዳር ዋናው መስሪያ ቤት መሆኑን እንገልፃለን ።

አድራሻ: -

ውሀ ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት

ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 የድሮው አዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊት

ፓ.ሣ.ቁ 106

ስልክ ቁጥር 0582221479

ባህርዳር

የውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-11-09
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20 ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-09 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20 ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Water Works Corporation
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 1,000 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 20, 2026)
  • Posted at: 2026-10-20T14:35:24.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders