Stationery

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነቀምት ሪጅን ጽ/ቤት የጽሕፈት መሣሪያዎችና ተያያዥ ዕቃዎች (ሎት 1) እንዲሁም የፕሪንተር ቶነር፣ የኮፒ ማሽን ቶነር እና የፕሪንተር ድራም ዩኒት (ሎት 2) ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጽሕፈት መሣሪያዎችና ተያያዥ ዕቃዎችን፣ የኘሪንተር ቶነር፣ የኮፒ ማሽን ቶነር እና የፕሪንተር

ድራም ዩኒት (Drum Unit) ግዥ ለመፈጸም የወጣ ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማሰታወቂያ

የጨረታ ቁጥር EEU/NR/NCB/04/2019

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነቀምት ሪጅን ጽ/ቤት በያዘው በጀት ዓመት የጽሕፈት መሣሪያዎችና ተያያዥ ዕቃዎችን፣ የፕሪንተር ቶነር፣ የኮፒ ማሽን ቶነር እና የፕሪንተር ድራም ዩኒት (Drumn Unit) ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. የጨረታው ሎት እና የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት

የዕቃው ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ (CPO)

ማስታወሻ

1

የጽሕፈት መሣሪያዎችና ተያያዥ የቢሮ ዕቃዎች ግዥ

80,000 ብር

 

በሲፒኦ (CPO) ወይም በባንክ ጋራንቲ

 

2

የፕሪንተር ቶነር፣ የኮፒ ማሽን ቶነር እና የፕሪንተር ድራም ዩኒት ግዥ

100,000 ብር

 

በሲፒኦ (CPO ወይም በባንክ ጋራንቲ

 

2, የተጫራቾች መስፈርት እና መሟላት የሚገባቸው ሰነዶች፡-

1.1 ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

1.2 በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ https://epg.ppa.gov.et ድረ-ገጽ ላይ የአቅራቢዎች ዝርዝር (EGP System / Supplier list) ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

1.3 ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስክ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት ከ2:00–6:00 ፣ከሰዓት ከ7:00–11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2:00–6:00 ዘወትር በሥራ ሰዓት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነቀምት ሪጅን ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 300 በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሂሳብ ቁጥር 1000254184784 ላይ ግቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

1.4 ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የተጠቀሰውን ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (Unconditional Bank Guarantee) ለ EEU NEKENETE REGION ተከፋይ አድርገው ማቅረብ አለባቸው።

1.5 ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የቴክኒከ እና የፋይናንሻል “ኦሪጅናል” እና “ኮፒ” በማለት በሁለት በተለያዩ እና በታሸጉ ኤንቨሎፖች በማዘጋጀት እንዲሁም ሲፒኦ (CPO) ኦሪጅናል ቴክኒካል ሰነድ ዉስጥ በማድረግ እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

1.6 ጨረታው ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል።

1.7 ማሳሰቢያ፡ መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

1.8  አድራሻ፡ ኦሮሚያ ክልል ፤ነቀምት ከተማ፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኩምሳ ሞሮዳ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት ወይም ቶታል ማደያ አጠገቡ ያለው መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሕንፃ ላይ ይገኛል፡፡

ስልክ ቁጥር፡ 0576602015/0911570832/0911564806]

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነቀምት ሪጅን


Tender details

  • Deadline: 2026-11-05
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-11-05 14:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ethiopian Electric Utility
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 20, 2026)
  • Posted at: 2026-10-20T16:13:00.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders