Stationery
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የሀሰና አገር ከፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ለክፍለ ከተማ መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሆን እቃዎች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesCleaning and Janitorial Equipment and Service
Amhara
More tags
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice FurnitureFurniture and FurnishingHouse FurnitureTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsSpare Parts and Car Decoration MaterialsAmharic2merkatoሀሰና አገር ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
Description
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የሀሰና አገር ከፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ለክፍለ ከተማ መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሆን
- ሎት1 የጽሕፈት መሳሪያ፣
- ሎት 2 የጽዳት እቃ፣
- ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃ፣
- ሎት 4 ቋሚ እቃ (ፈርኒቸር)፣
- ሎት 5 የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅና አልባሳት፣
- ሎት 6 የደንብ ልብስ ጫማ፣
- ሎት 7 የተሽከርካሪ መለዋወጫእቃ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በአዲስ ዘመን ጋዜጣላይ ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም የወጣውን ማስታወቂያ በማየት የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ
በዚህም መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ። መሆኑን እገልጻለን።
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ያለው።
- የግዥ መጠኑ ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
- በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ከፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታመክፈቻው ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጂናል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ላሉት ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በC.PO ብቻ የጠቅላላ ዋጋውን 1% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ፤ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻው ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ጸንቶ ይቆያል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኮምቦልቻ ከተማ ሀሰና አገር ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በመምጣት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከጥቅምት 10/2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት 11፡30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጂናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ሀሰና አገር ክ/ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ከ10/02/2019 ዓ.ም እስከ 20/02/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ። የጨረታ ሳጥኑ በቀን 20/02/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል። ይሁን እንጂ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ከሆነ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው የመከፈቻ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታ ውድድሩ የሚካሄደው በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም፤ ያልተሞላ ዓይተም ከተገኘ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ጨረታውን ካወጣው መስሪያ ቤት ጋር ከጨረታ መክፈቻው ከ 5 ቀን በፊት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 75 85 40 15 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መደረግ ይኖርበታል። ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ጊዜ በኋላ ለ40 ቀናት ይሆናል።
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆኑ፣ ለወደፊቱም በመስሪያ ቤቱ ግዥ የማይሳተፉና ያስያዙት የጨረታ ማስበሪያ የሚወረስ ይሆናል።
- ግዥ ፈጻሚው አካል ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊው ተጫራች በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ እስከ 20% (ሃያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል ይሆናል።
- ለሎት 5 እና ለሎት 6 አሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች ግዥ ፈጻሚ መስሪያ ቤት በሚያቀርበው ናሙና ወይም ሳምፕል መሰረት የሚያቀርቡ ይሆናል።
- ከሎት 5 እና ከሎት 6 ውጭ ያሉ ሎቶች ላይ መስሪያ ቤቱ ሳምፕል ያስፈልጋቸዋል ብሎ የሚያምንባቸው አይተሞችን በሚቀርበው ናሙና ወይም ሳምፕል መሰረት የሚያቀርቡ ይሆናል።
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ሀሰና አገር ክፍለ ከተማ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- ክፍለ ከተማው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሀሰና አገር ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-30
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-30 10:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: ሀሰና አገር ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
- Bid bond: 1% ለእያንዳንዳቸው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 20, 2026)
- Posted at: 2026-10-20T16:30:31.000Z
- Source: Qelal Tenders