House and Building Sale
የቦታ ስፋት 59.07 ካ.ሜ የሆነ የንግድ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍባለመብት ሳምሶን ጉሉማ እና በፍ/ባለዕዳ መስፍን ታደሰ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/212091 በ1/8/2018ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/216282 በ29/10/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በሻሌ ሳይት ብሎክ 26 የሚገኝ የካርታ ቁጥር ለ/ኩ/18/8/3/162568/00 በፍ/ባለዕዳ ስም የተመዘገበ ቤት የሴሪያል ቁጥር 1682364 የተመዘገበ ካርታ ያለው የቦታ ስፋት 59.07 ካ.ሜ የቤቱ አገልግሎት በካርታቸው መሰረት የንግድ ቤት የሆነ ቤቱ የንግድ ቤት ስለሆነ በገቢዎች ቢሮ መመሪያ መሰረት ካፒታል ጌይን የሚከፈል የሆነ የሀራጅ መነሻ ዋጋ 2,325,113 (ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሃያ አምስት ሺህ አንድ መቶ አስራ ሶስት) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል ካፒታል ጌን ግራ ቀኙ የሚከፍሉ መሆኑ ታውቆ ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበውትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ _ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ ዳይሮክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድበሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-24
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-11-24 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Oct 21, 2026)
- Posted at: 2026-10-21T13:00:43.000Z
- Source: Qelal Tenders