Stationery
አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) የተለያዩ የፅህፈት መሣሪያዎች (ሎት 1) እና የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች (ሎት 2) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ /አ.ማ/
የፅህፈት መሣሪያዎች ፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር AIC፡-0018/2026
ኩባንያችን የተለያየ መጠን ያላቸውን የፅህፈት መሣሪያዎች እና የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሀ. ሎት -1 የፅህፈት መሣሪያዎች
- ለ. ሎት-2 የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እንዲሁም ከሚመለከተው የመንግስት ተቋም የብቃጥ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጨረታው አሸናፊ ባቀረበው ሰነድ መሰረት እቃዎቹን ሳያቀርብ ቢቀር ያስያዘው በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል ወይም ተመላሽ አይሆንም።
- ከላይ በተራ ቁጥር 2 ላይ የተገለጸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ሲፒኦ (CPO) ሙሉ ለሙሉ ተመላሽ የሚሆነው አሸናፊው ድረጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች ለኩባንያው ገቢ ካደረገ በኋላ ኩባንያው የገቡትን እቃዎች በሳምፕላቸው መሰረት መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኩባንያው ዋና መ/ቤት በመገኘት የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆን ወይም አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ድረስ ቦሌ በሚገኘው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋና መ/ቤት ህንፃ 11ኛ ፎቅ በስራ ሰዓት በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ህንፃ 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የስብሰባ/ስልጠና አዳራሽ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚያስገቡት የጨረታ ሰነድ የእቃው ዝርዝር መግለጫ (Specification) የያዘ ሊሆን ይገባል እንዲሁም በሚያቀርቡት ናሙና (Sample) ላይ የድርጅታቸው ማህተም ሊኖር ይገባል።
- አንዱ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት ከጨረታው የሚያሳግድ መሆኑን እንገልፃለን።
- አሸናፊው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀለት ወይም የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች ከ7 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ወይም በውሉ መሰረት ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች ሲወዳደሩ ባስገቡት (ባቀረቡት) ሳምፕል / ናሙና መሰረት መሆን አለበት።
- ተጫራቶች ያሸነፉትን እቃዎች የኩባንያው ዋና መ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ በከፊል ወይም በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 011 661 1877 / 011 663 7485 / 011 663 7716 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ድርድይ አካባቢ አፍሪካ ኢንሹራንስ ህንፃ 1
Tender details
- Deadline: 2026-10-27
- Bid closing time: 14:30
- Bid opening: 2026-10-27 15:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Africa Insurance Company
- Buyer's registered address: ቦሌ ጃፓን ኤምባሲ አካባቢ
- Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር)
- Bid document price: 400 (አራት መቶ ብር)
- Published on: Reporter (Oct 21, 2026)
- Posted at: 2026-10-21T14:26:05.000Z
- Source: Qelal Tenders