Wood and Wood Working
የሚዛን ገጠር ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ማዕከል የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ/ኢት/ሕዝ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ የሚዛን ገጠር ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት ለሚያመርታቸው ምርቶች አገልግሎት የሚውሉ በካፒታል እና በመደበኛ በጀት
- ሎት 1. የተለያዩ መጠን ያላቸው የሀገር ውስጥ ጣውላዎች ጥድ
- ሎት 2. የሕንፃ መሣሪያዎች
- ሎት 3. የተለያዩ ብረታ ብረቶች
- ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት 5. የቢሮ ወንበሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተለውን መስፈርት ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የተሰማሩበትን የሥራ ዘርፍ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
- ተጫራቾች የተሠማሩበት የሥራ ዘርፍ ጋር በተያያዘ ለተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ በሚመለከተው አካል የተሰጠው የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ቼክ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ለሚዛን ገጠር ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ማዕከል በማለት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ለጣውላ ጨረታ 5000 /አምስት ሽህ ብር ብቻ
- የሕንፃ መሣሪያ ጨረታ 1000 /አንድ ሽህ ብር ብቻ
- የብረታ ብረት ጨረታ 1000 /አንድ ሽህ ብር ብቻ
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጨረታ 800 /ስምንት መቶ ብር/ብቻ
- ለፈርኒቸር ግዥ ጨረታ 800 /ስምንት መቶ ብር/ ብቻ
6. የጨረታ አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ጥራትና ደረጃን የጠበቀ እቃዎች እስከ ግዥ ፈጻሚው መሥሪያ ቤት ድረስ በራሳቸው ወጪ በተገባው ውል መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. የተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በተቋሙ ግዥና ክፍያ ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይቻላል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎኘ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ15ተኛው የሥራ ቀን 11፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ተኛው ቀን 3፡30 ሰዓት በመሥሪያ ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።
10. መሥሪያ ቤቱም የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 13 85 50 54 ወይም 09 13 65 14 40 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
12. በጨረታው ማስታወቂያ ላይ የትርጉም ለውጥ ቢኖር በጨረታው ሰነድ የተገለጸው ተቀባይነት ይኖረዋል።
የሚዛን ገጠር ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ማዕከል /ሚዛን አማን/
Tender details
- Deadline: 2026-11-07
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ15ተኛው የሥራ ቀን 11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-09 09:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ16ተኛው ቀን 3፡30 ሰዓት
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: Mizan Rural Technology Promotion Center
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 22, 2026)
- Posted at: 2026-10-22T09:05:49.000Z
- Source: Qelal Tenders