Stationery

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ጽ/መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና አድቫስድ የኢኮቴ ባለሙያዎች ሥልጠና ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ

  • በሎት1 ፣ ጽ/መሳሪያ ግዥ፣
  • በሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ ግዥ እና
  • በሎት 3 አድቫስድ የኢኮቴ ባለሙያዎች ሥልጠና ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

  1. የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT / ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
  3. በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡና በህግ ያልተገደቡ ፤
  4. በሎት 1 ጽ/መሳሪያ ግዥ፣ በሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ ግዥ እና በሎት 3 አድቫስድ የኢኮቴ ባለሙያዎች ሥልጠና ግዥ ለመፈፀም በቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት በቢሮ የግዥ ፋይ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በመቅረብ 300 ብር በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በስም በታሸገ ኢንቬሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንስ የጨረታ ሰነድን ለብቻ ለብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለተዘጋጀ የቴክኒክና የፋይናስ ሰነድ ተጨማሪ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኢንቬሎፑ የውጭ ገጽ ዋና ኦርጂናል ወይም / ኮፒ/ ብሎ በመፃፍ አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. በማንኛውም ኤንቬሎፕ ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ ማስገባት የለባቸውም ስለ ተጫራቾች የንግድ ፈቃድ የቫት ሰነድ መልካም አፈጻጸም ወዘተ መካተት ያለባቸው በቴክኒክ የጨረታ ሰነድ በሆነት በዋናው ኦሪጅናል እና ኮፒ ተብሎ በተገለጹት በሁለቱም ኤንቬሎፕ ሲሆን በፋይናንስ የጨረታ ሰነድ በዋናው ኦሪጅናል | ሆነ ኮፒ ኤንቬሎኘ ውስጥ ከፋይናንስ የጨረታ ሰነድ ውጭ ምንም ተጨማሪ መረጃ ማስገባት አይፈቀድም፤
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በዕለቱ 8፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል። የሚከፈትብት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል።
  8. ማንኛውም ተጫራች ህጋዊ ወኪል በፍርድ ቤት የተረጋገጠና በኢፌዴሪ በክልሉ መንግስት ህጐች ተቀባይነት ያለው ኦሪጅናል የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት ፎቶ ኮፒ ተደርጐ ብቻ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% በባንክ የተረገገጠ ሲፒኦ/ Letter of credit ለብቻው በታሸገ ፖስታ መሆን አለበት።
  10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ/ጉ/አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር 046 771 0711 ዘወትር በስራ ሰዓት መጠየቅ ይችላሉ።
  11. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው
  12. በሎት 1 ጽ/መሳሪያ ግዥ፧ በሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ ግዥ እና በሎት 3 አድቫስድ የኢኮቴ ባለሙያዎች ሥልጠና ግዥ ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተያያዘና የተገለጸ በመሆኑ ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ። የቢሮ አድራሻ፡- በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወረቤ ቅርንጫፍ ህንፃ ላይ ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-07
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-07 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Innovation and Technology Agency
  • Buyer's registered address: አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 6 አምስት ኪሎ ቅድስተማርያም ቤተክርስቲያን ገባ ብሎ አዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ክፍል
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 300 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 22, 2026)
  • Posted at: 2026-10-22T11:09:22.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders