House and Building Foreclosure
የቦታ ስፋት 1000 ካሬ ሜትር የመኖሪያ ቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
House and Building ForeclosureSales, Disposals and ForeclosureHouse and Building Sale
Sidama
More tags
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በአፈፃፀም ከሳሾች እነ ወ/ሮ ሮቢት ኤርሚያስ 9 (ስዎች) እና በአፈፃፀም ተከሳሾች እነ አቶ ብርሃነ ተክሌ 4 (ስዎች)መካከል ስላለዉ የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በሀዋሳ ከተማ ሀይቅ ዳር ክ/ከተማ ገበያ ዳር ቀበሌ ውስጥ በሟች ወ/ሮ ሙሉ ተክሌ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በካርታ ቁጥር D269A270 የቦታ ስፋት 1000 ካሬ ሜትር የመኖሪያ ቤት ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የመና/ከ/ከ/ልማትና ኮ/ን/ጽ/ቤት በላኩት መነሻ ግምት ዋጋ ብር 4,786,400.00 (አራት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ብር) ሆኖ በሐራጅ እንዲሸጥ እና የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ 09/02/2019ዓ/ም ጀምሮ እስከ 09/03/2019ዓ/ም ለ30 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ የሀራጅ ሽያጩ በ10/03/2019ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ በሐራጅ እንዲሸጥ ተወስኗል።
ስለሆነም፡-
- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎች ለጨረታው ማስከበሪያ የመነሻ ዋጋውን 1/4ኛ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሒደት ቢሮ ቁጥር 030 በአካል ቀርባችሁ በማስያዝ እና ያስያዛችሁበትን ሕጋዊ ደረሰኝ ይዛችሁ በመቅረብ ጨረታውን መሳተፍ ትችላላችሁ።
- ቀርባችሁ በማስያዝ እና ያስያዛችሁበትን ሕጋዊ ደረሰኝ ይዛችሁ በመቅረብ በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ::
- በጨረታው ለተሸነፈ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስለታል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን የጨረታ ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- ያሽነፈበትን የጨረታ ገንዘብ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ ካላደረገ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ በድጋሚ ማስታወቂያ ወጥቶ ጨረታ ይካሔድበታል።
- ጨረታውን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የስም ዝውውር በፍ/ቤቱ ትእዛዝ ይፈፅምለታል፡፡ የጨረታው ሒደት የሚካሔደው 10/03/2019ዓ/ም 4፡00 – 6፡00 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ከተማ ሀይቅ ዳር ክ/ከተማ ገበያ ዳር ቀበሌ ውስጥ በሟች ወ/ሮ ሙሉ ተክሌ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ቅጥር ግቢ እንደሆነ አውቀው በተባለው ጊዜ እንድትገኙ ፍ/ቤቱ አዟል።
የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-19
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-11-19 12:00
- Region: Sidama
- Publishing entity: Hawassa City High Court
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Oct 22, 2026)
- Posted at: 2026-10-22T12:57:41.000Z
- Source: Qelal Tenders