Cleaning and Janitorial Equipment and Service
የእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎች እና ሥራዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/19
የእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች
2. የፅዳት ዕቃዎች፣ የእንስሳት መኖ
3. የጽሕፈት መሣሪያዎች
4. የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፌት
5. የሕትመት ሥራዎች
6. የተለያዩ የስጦታ ዕቃዎች
7. የጥገና ዕቃዎች
8. የሕክምና ቋሚና አላቂ ዕቃዎች
9. የተለያዩ ማጣቀሻና ፊክሽን መጽሐፎች፣ የስፖርት ዕቃዎች፣ ቤተ-ሙከራ ዕቃዎች
10. የመኪና ዕቃዎች
11. የማሽነሪ ዕቃ ጥገና እና ሰርቪስ
12. የእንስሳት ሕክምና
13. የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ኪራይ መኪና
14.በት/ቤት ግቢ ውስጥ የተለያዩ የጥገና ሥራዎች
ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት ማሟላት አለባቸው።
1. ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
2. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ተጨማሪ እሴት ታክስ(ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ እና ከፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶሰት መቶ ብር) በየሎቱ ከት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 103 መግዛት ይችላሉ። ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት 1ኛ ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል፣ ኮፒውን እና (CPO) በሶስት ፖስታ ለየብቻ ታሽጎ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 106 ማስገባት ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ጨረታው እስከሚከፈት ድረስ የዕቃ ናሙና መቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. አሸናፊው በሚያቀርባቸው ዕቃዎች ላይ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
5. ጨረታው 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 106 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች ት/ቤቱ ባቀረበው የዋጋ መሙያ ብቻ በመሙላት ማቅረብ እና ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ት/ቤቱ የሚገዛውን ዕቃ ብዛት 20% የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት(1) ብር 100,000 ለሎት (2) ብር 50,000 ሎት (3) ብር 50,000 ለሎት (4) ብር 50,000 ለሎት (5) ብር 50,000 ለሎት (6) ብር 50,000 ለሎት (7) ብር 50,000 ለሎት (8) ብር 50,000 ለሎት (9) ብር 50,000 ለሎት (10) ብር 20,000 ለሎት (11) ብር 20,000 ለሎት (12) ብር 5,000 ለሎት (13) ብር 20,000 ለሎት (14) 50,000 በባንክ የተረጋገጠ (CPO) በታሸገ ፖስታ ብቻውን ማቅረብ አለባቸው።
9. ጥቃቅንና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች የሚወዳደሩት በሚያመርቱት ምርት ካልሆነ በስተቀር ዕቃ ገዝተው የሚያቀርቡ ከሆነ እንደማንኛውም ተጫራቾች ሰነድ በመግዛትና ሲፒዮ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
10. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. በጨረታ የሚሳተፉ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ (ማብራሪያ) ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 011 126 1615 / 011 122 4954 በመደወል ማግኘት ይችላሉ። እንዲሁም የሚሠሯቸውን ሥራዎች በሙሉ በአካል ት/ቤቱ በመገኘት ሳንፕል መውሰድ ማየት ይችላሉ።
12. ተጫራቾች በአንድ የዕቃ አይነት በአንድ ብራንድ ብቻ መወዳደር ይኖርባቸዋል።
13. የጥገና ሥራዎች ጥሩ አፈጻጸም ያላቸው ቢያንስ 3 የምስክር ወረቀት ማቅረብ እና የበጀት ዓመቱ ማጠናቀቅያ ክሊራንስ ማቅረብ ግዴታ ነው።
አድራሻ፡- እቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ት/ቤት ከ6 ኪሎ ዩኒቨርሲቲ በግራ በኩል በሚወስደው መንገድ ወይም ምስካዬ ኅዙናን መድኃዓለም ቤተከርስቲያን ፊት ለፊት ገባ ብሎ ይገኛል።
የእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-04
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት 1ኛ ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-04 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት 1ኛ ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: እቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ት/ቤት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር በየሎቱ
- Published on: Addis Zemen (Oct 23, 2026)
- Posted at: 2026-10-23T08:38:00.000Z
- Source: Qelal Tenders