Sport Materials and Equipment
የአምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል የስፓርት ትጥቆችና የስልጠና ቁሳቁሶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
2ኛ የጨረታ ማስታወቂያ
የአምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ በማዕከሉ ለሚያሠለጥናቸው ሠልጣኞችና አሠልጣኞች የተለያዩ የስፓርት ትጥቆችና የስልጠና ቁሳቁሶች የክልሉ መንግሥት ባወጣው የግዢ አዋጅ ቁጥር 157/2002 በመከተል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ዝርዝር ሁኔታዎች
ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ : ስለ እስፓርት ትጥቆች የሚገልጽ ዝርዝር ሰነድ ዶክመንት/ የማይመለስ ሁለት መቶ (200) የእትዮጵያ ብር በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት በአምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ በጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
የተጫራቾች ግዴታ
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ከሆኑ፤ ተመዝጋቢ ስለ መሆናቸው የሚገልጽ ማሥረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ የሚችሉ።
- የታደሰ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸውና ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ የኢትዮጵያ ብር 1% በCPO በ ሲንቄ ባንክ በማስገባት የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በአገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በአቅራቢነት የተመዘገቡና ሰርተፍኬት ያላቸው እና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ኮፒና ዋናውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት 13/02/2019 እስከ 03/03/2019 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት በአምቦ እግር ኳስ ማሠልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይችላሉ። ከላይ በተገለጸው መሥሪያ ቤት አዳራሽ ውስጥ በ 16ኛው ቀን በ 04/03/2019 ከቀኑ 4 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት (ባይገኙበትም) በ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- አሸናፊው ድርጅት ማናቸውንም አስፈላጊ ወጭዎች ችሉ ያሸነፈባቸውን የስፓርት ትጥቆችና ቁሳቁሶች በሰዓቱ በማዕከሉ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ማዕከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 260 9010 ፣ 09 13 28 68 68 ወይም 11 260 2341 አምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የአምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል
Tender details
- Deadline: 2026-11-13
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-11-13 10:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Ambo Football Training Center
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 23, 2026)
- Posted at: 2026-10-23T09:22:50.000Z
- Source: Qelal Tenders