Personal Care Products and Services
ጣምራ ለማህበራዊ ልማት ድርጅት በሲዳማ እና በኦሮሚያ ክልል እየተገበረ ለሚገኘው ICD ፕሮጀክት የሚውል የተፋሰስ ሥራ ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች እና የግል ደህንነት መጠበቂያ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ጣምራ ለማህበራዊ ልማት ድርጅት ከተመሠረተበት 1990 ዓ.ም ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 29 ዓመታት በወጣቶች ልማት፣ በሥነ-ተዋልዶ ጤና፣ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሰውን ጾታዊ ጥቃት በመከላከል፣ በአካባቢ ጥበቃና የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭትና በሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ዙሪያ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ክልሎችና በአዲስ አበባ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ለዚህም ተግባሩ ድርጅታችን ላበረከተው የማኅበረሰብ አቀፍ ጉልህ አስተዋኦ ከሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር፣ ከኦሮምያ ክልልና ከኢፊዲሪ መንግስት የሠርትፍኬት፣ የዋንጫ፣ የቦታና የመኪና ሽልማቶችን ያገኘ አንጋፋ ድርጅት ነው፡፡
ድርጅታችን ጣምራ ለማበራዊ ልማት ድርጅት በሲዳማ እና በኦሮሚያ ክልል እየተገበረ ለሚገኘው ICD ፕሮጀክት የሚውል የተፋሰስ ስራ ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች እና የግል ደህንነት መጠበቂያ እቃዎች ግዢ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የዚህን ጨረታ ዝርዝር የያዘውን ዶክመንት የማይመለስ 200 ብር በመክፈል፤ የጨረታ ሰነድ መግዛት እና ጨረታውን መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን ተጫራች ድርጅቶች ተወካይ መላክ የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
አድራሻ - አዲስ አበባ፣ቦሌ፣ወረዳ 07, ከሰአሊተ ምህረት ወደ ጃክሮስ በሚወስደው መንገድ፣ከመጀመሪያው የትራፊክ መብራት ቀጥሎ ከ አቢሲኒያ ባንክ ጀርባ
ለበለጠ መረጃ - +251 982024874 ይደውሉ፡፡
Deadline – ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም (October 30, 2026)
Tender details
- Deadline: 2026-10-30
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-10-30 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tamra Economic Development Organization
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Qelal Tenders (Oct 23, 2026)
- Posted at: 2026-10-23T12:42:42.000Z
- Source: Qelal Tenders