House and Building Sale
የቦታ ስፋት 57.55 ካ.ሜ. የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እንጋቱ መገርሳ እና የፍባለዕዳ መስታወት መሊሳ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/119291 በሚያዚያ16 ቀን 2018 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ 126258 በግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአቃቂ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ውስጥ የሚገኝ የካርታ ቁጥር 0943/A/1/A/3 ተመዝግቦ የሚገኝ የይዞታ መለያ ቁጥር AA000070804432 የተመዘገበ ካርታ ያለው የቦታ ስፋት 57.55 ካ/ሜ በወ/ሮ መስታወት ሙሊሳ ስም የተመዘገበ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 2,127,048 (ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ ሃያ ሰባት ሺህ አርባ ስምንት ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡3ዐ ብቻበመግኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንሰፖርት ንብረቱን ባበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለሙብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የነበረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በተረጋገጠ C.P.O ማሰያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት/ ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ብቻ መሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ, ማድረግ አለበት። የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852
በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ
እፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-25
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-11-25 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Oct 24, 2026)
- Posted at: 2026-10-24T08:57:25.000Z
- Source: Qelal Tenders