Equipment and Accessories

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 8 ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የዳግማዊ ቴዎድሮስ መጀ/ደ/ት/ቤት ለ 2019 ዓ.ም ዓመት በጀት እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት እና መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 8 ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የዳግማዊ ቴዎድሮስ መጀ/ደ/ት/ቤት ለ 2019 ዓ.ም ዓመት በጀት አገልግሎት ላይ የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት እና መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 ቋሚ እቃ 2000
  • ሎት 2. የደንብ ልብስ እና የስፌት አቅርቦት 3000፣
  • ሎት3. የፅዳት እቃዎች 2500፣
  • ሎት 4. የፅሕፈት መሣሪያዎችና አላቂ የቢሮ እቃዎች 2000
  • ሎት 5. የእስፖርት ማቴሪያል እቃ 1000፤
  • ሎት 6. የህትመት ውጤቶች 1000፤
  • ሎት 7. የሕክምና እቃዎችና መድኃኒት 1000
  • ሎት 8 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች 1000፣
  • ሎት 9 የግንባታ እቃዎች 1000፣
  • ሎት 10 ለፕላንት ለማሸነሪ ጥገና እና እድሳት 1000፣
  • ሎት 11 ለመስተንግዶ የሚሆን አቅርቦት (ውሃ ቆሎ.....) 500 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ለመግዛትና ማሠራት ይፈልጋል።

ተጫራቾች በጨረታ መወዳደር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1- የምዝገባ ፍቃድ የዘመኑ ግብር የከፈሉና ንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት (Tax) ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2- ተጫራቾች ማንኛውንም የመንግሥት ታክስና የግብር ግዴታዎች ከነመጓጓዣው በሚያቀርቡበት የመወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውስጥ አካተው ማቅረብ አለባቸው።

3- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሞልተው ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ በዳግማዊ ቴዎድሮስ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ከ 05-2% የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4- የጨረታ ሰነድ በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል በግንባር በማቅረብ ለዚሁ የተዘጋጀውን ሰነድ ብር 200 ብር በመክፈል መውሰድም ይኖርባቸዋል።

5- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን እቃ ሳንፕል ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ሳንፕል ለማይቀርብባቸው የቋሚ የዕቃ አይነቶቸ ት/ቤቱ በሚያቀርበው እስፔስፍኬሽን መሰረት መሙላትና የፎቶ ሳንፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6- በጥቃቅንና አነስተኛ ለሚመጡ ተጫራቾች ማምረት በሚችሉበት ብቻ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ማምረት በማይችሉበት እቃዎች የጨረታ ስነድ እንደ ማንኛውም ተጫራች ገዝተው መወዳደር ይችላሉ። ከተደራጁበት ተቋም (መንግሥታዊ) የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸል።

7- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የምዝገባ ፍቃድ፣ ቫት፣ ቲን፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ ንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱና የዋጋ ዝርዝራችውን አንድ ኦርጅናል ፋይናሻል አንድ ቴክኒካል አንድ ኮፒና የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ሦስቱም በተለያዩ ፖስታዎች ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በት/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሙሉ የጨረታውን ሰነድ በመሙላትና በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ሙሉ የጨረታ ሰነድ ተመላሽ ማድረግ ይኖርባቸዋል ሙሉ የጨረታ ሰነድ ተመላሽ ያላደረገ ከጨረታው ይሰረዛል።

8- የጨረታሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ለተከታታይ 10 የሥራ ቀን አየር ላይ ይውላል በቀጣዩ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን በት/ቤቱ ቤተ/መፅሐፍት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ይከፈታል ተጫራቾች ጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታ ጨምሮ ጨረታው ይከፈታል። ቀጣዩ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀንይከፈታል። 

9- ተጫራቾች ያሽነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ወጪ ትምህርት ቤቱ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው። ተጫራቾች ያሽነፋባቸውን የሕክምና ዕቃ በባለሙያ ታይቶ የሚገባ መሆኑን እናሳውቃለን።

10 - አሸናፊው ተጫራች ዕቃውን ከማስገባቱ በፊት ከት/ቤቱ ጋር ውል በመፈፀም ውል ማስከበሪያ የዕቃውን 10% በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

11- የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሑፍ በደብዳቤ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን። አሸናፊው ድርጅቶች አሸናፊ መሆኑን በደብዳቤ ከተገለጸለት በኋላ በሰባተኛው ቀን ውስጥ ቀርቦ ውል መዋዋል አለበት።

12. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ሊስት ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገጽ WWW.pagov.et  ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው አድራሻ:- ከአዲስ ከተማ መሰናዶ ት/ቤት ፊት ለፊት 200 ሜትር ገባ ብሎ
ለበለጠ መረጃ፤ - በስልክ ቁጥር 011 213 0608 ደውለው መጠየቅ ይችላል
የዳግማዊ ቴዎድሮስ መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-05
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ለተከታታይ 10 የሥራ ቀን አየር ላይ ይውላል በቀጣዩ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-05 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ለተከታታይ 10 የሥራ ቀን አየር ላይ ይውላል በቀጣዩ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን በት/ቤቱ ቤተ/መፅሐፍት ከጠዋቱ 4፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Dagemawi Tewoderos Elementary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 24, 2026)
  • Posted at: 2026-10-24T09:16:49.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders