Tri Wheeler, Motorcycles and Bicycles Purchase
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ ሞተር ሳይክል (150 cc) ከነአክሰሰሪዎቹ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የሞተር ሳይክል( 150 cc) ከነአክሰሰሪዎቹ ግዥ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 85/2019
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የቀረበውን ለዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮግራም (SLMP-V) የሞተር ሳይክል (150 cc) ከነአክሰሰሪዎቹ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የሚከፈትበት ሰዓት |
መክፈቻ ቦታ |
|
1 |
የሞተር ሳይክል (150 cc) ከነ አክሰሰሪዎቹ
|
በቁጥር
|
20
|
200.000
|
በ31ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡10 ይከፈታል
|
ዲላ መምህራን ኮሌጅ ጊቢ (ግብርና ቢሮ) ግዥ ን/አስ ዳይሬክቶሬት ክፍል |
በመሆኑም በንግድ ሥራ ዘርፉ የታደሰ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ በአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት የሚያቀርብ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃዎች ያላቸውና የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፤ በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ያስያዙበትን ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው ተከታታይ 30ኛ ቀናት እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል በዲላ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ ትትስ ግቢ ከሚገኘው የመ/ቤቱ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነድ መሙላት ይህ የጨረታ የቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦርጅናልና አንድ ኮፒ የመጫረቻ ሰነዶችን በአንድ እናት በፖስታ በማዘጋጀት በ31ኛው ቀን በቢሮው ግዥና ንብ/አስ/ዳይ ቢሮ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች ተወካዮቻቸው በተገኙበት በቢሮው የግዥና ንብ/አስ/ዳይ/ቢሮ ይከፈታል
- ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20 ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
አሸናፊ የሆነው ተጫራች ከመ/ቤቱ ጋር ውል ለመፈራረም ሲቀርብ የውሉን ዋጋ ቢያንስ 10% ውል ማስከበሪያ ዋስትና በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና፣ በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ አለባቸው። - ከ200,000 ሺህ በላይ ለሆነ ግዥዎች ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- የጨረታው ሳጥን መክፈቻ በ31 ኛው ቀን የመንግሥት የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣይ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
- ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ 046 131 0134 ይጠቀሙ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-11-23
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ31ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-23 10:10
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ31ኛው ቀን 4፡10 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: South Ethiopia's Regional State Agriculture Bureau
- Bid bond: 200.000 ብር
- Bid document price: 300.00/ሶስት መቶ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Oct 24, 2026)
- Posted at: 2026-10-24T09:57:07.000Z
- Source: Qelal Tenders